በድባጤ ወረዳ ከጋሌሳ ወደ አዊ ዞን ቻግኒ መስመር ሲጓዝ በነበሩ ሁለት የጭነት መኪናዎች ላይ ዝርፊያና ቃጠሎ እንደተፈፀመባቸው ተገለፀ። አሻራ ሚዲያ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም…

በድባጤ ወረዳ ከጋሌሳ ወደ አዊ ዞን ቻግኒ መስመር ሲጓዝ በነበሩ ሁለት የጭነት መኪናዎች ላይ ዝርፊያና ቃጠሎ እንደተፈፀመባቸው ተገለፀ። አሻራ ሚዲያ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም ባህርዳር_ኢትዮጵያ መስከረም 4 ቀን 2014 በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ከጋሌሳ ቀበሌ ተነስተው ወደ አዊ ዞን ቻግኒ ሲጓዙ በነበሩ ሁለት መርቼዲስ የጭነት መኪናዎች ላይ በተላላኪው የጉምዝ ታጣቂዎች ቡድን ዘረፋና ቃጠሎ የደሰሠ ሲሆን በቆሎ እና ቡና መጫናቸው የተነገረላቸው ሁለቱም ተሽከርካሪዎች በድባጤ ወረዳ ቂዶህ እንደደረሱ በጭቃ መያዛቸውን ተከትሎ ወደ ኋላ መዘግየታቸው ተገልጧል። በሌላ መኪና አብረዋቸው ወደ ቻግኒ ሲጓዙ የነበሩ ባለስልጣናትና አጃቢዎቻቸው ጥለዋቸው መሄዳቸውን ተከትሎ ነው ትናንት አመሻሹን የጉምዝ ታጣቂዎች የዝርፊያና የቃጠሎ ሰለባ የሆኑት ተብሏል። ሁለቱም ሾፌሮች ከአደጋው መትረፋቸውም ተገልጧል። ወደ አካባቢው የገቡ የልዩ ኃይል አባላትም በቂ የሆነ ትዕዛዝ እየተሰጣቸው ባለመሆኑ ጨካኙን ቡድን በመቅጣት ወገናቸውን ለመታደግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በከተማ ዙሪያ ብቻ የተገደበ ነው ያሉት ነዋሪዎች አስቸኳይ እርምት እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል። አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 Telegram :-https://t.me/asharamedia24 Yotube:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply