በድብቅ ለህወሓትሊደርስ የነበርው ገንዘብ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 ለህወሓት ሊደርስ ነበር የተባለ 3 ሚሊዮን ብር በቆቦ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለ:: በቆቦ ከተማ ለአሸባሪው ህወሓት ሊደርስ እንደነበር የተጠረጠረ 3 ሚሊዮን ብር በቆቦ ከተማ ህዝብ እና በከተማው ፓሊስ እና ሕዝባዊ ሚሊሻ ሰራዊት አማካይነት በትናንትናው እለት መያዙ ተነግሯል ተጠርጣሪዎቹ ገንዘቡን ደብቆ ለማሸጋገር የተጠቀሙበት መንገድ ያልተጠበቀ ቢሆንም፥ የቆቦ ከተማ ህዝብ እና የፀጥታ ሀይሉ የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የቆቦ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ህብረተሰቡ ገንዘቡ እንዲያዝ ላደረገው አስተዋጽኦ ፖሊስ ምስጋናውን ማቅረቡን ከከተማዋ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply