በዶሮኒ ወረዳ ኦረቦ ቀበሌ ከነሃሴ 26/2014 ጀምሮ የገቡት የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን አባላትን የሚያስለቅቅ አካል ባለመገኘቱ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች እየተፈናቀሉ ነው። አማራ ሚ…

በዶሮኒ ወረዳ ኦረቦ ቀበሌ ከነሃሴ 26/2014 ጀምሮ የገቡት የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን አባላትን የሚያስለቅቅ አካል ባለመገኘቱ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች እየተፈናቀሉ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ በዶሮኒ ወረዳ ኦረቦ ቀበሌ ከነሃሴ 26/2014 ጀምሮ የገቡት የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን አባላትን የሚያስለቅቅ አካል ባለመገኘቱ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች እየተፈናቀሉ እና በየጫካው እየተሳደዱ መሆኑ ተገልጧል። በኦረቦ ቀበሌ ያሉ ወገኖችም የአስገድዶ መድፈር፣ መሳሪያ የመቀማት እና ንብረት የመዝረፍ ወንጀል እየተፈጸመባቸው ነው ተብሏል። በሽህ የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ አባላት አሁን ላይ በት/ቤት፣በፖሊስ ጣቢያ እና በስላሴ ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ይገኛሉ። በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን የዶረኒ ወረዳ ከጮራ፣ ከሳች አልጌ፣ ከኖፓ፣ ሁሩሙ እና ያዮ ወረዳዎች ይዋሰናል። ከጮራ እና ከያዩ በኩል የመንግስት ኃይል ቢመጣም ትዛዝ አልተሰጠንም በሚል ዝም ብሎ በቅርብ ርቀት ምሽግ ይዞ መተያየትን መርጧል ይላሉ። ስለዚህ የሚመለከተው የመንግስት አካል በአስቸኳይ ከጎናቸው በመሆን ህዝቡን ከስቃይ እና ከእንግልት እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply