በዶ/ር አቢይ ንግግር ውስጥ የታዩ እና ያልታዩ ሀገራዊ እውነቶች በወንድወሰን ተክሉ 👉  አጠቃላይ የንግግራቸው እድምታና ጭብጥ፦ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግ…

በዶ/ር አቢይ ንግግር ውስጥ የታዩ እና ያልታዩ ሀገራዊ እውነቶች በወንድወሰን ተክሉ 👉 አጠቃላይ የንግግራቸው እድምታና ጭብጥ፦ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግ…

በዶ/ር አቢይ ንግግር ውስጥ የታዩ እና ያልታዩ ሀገራዊ እውነቶች በወንድወሰን ተክሉ 👉 አጠቃላይ የንግግራቸው እድምታና ጭብጥ፦ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር ሁለት ኃያል ነጥቦችን እጅግ አጉልተውና ለጥጠው ያቀረቡ ሲሆን እነዚህ ሁለት ነጥቦችም ችግርን በተመለከተ በሀገራችን የተፈጸሙ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ሁሉ ምንጩና ባለቤት ህወሃት መሆኑን የገለጹበትና ይህንን ትግል ብቻውን በመታገል ለድል ያበቃው የእሳቸው ዶ/ር አቢይ አመራር ብቻ መሆኑን በመግለጽ ደምድመዋል፡፡ እንደ እሳቸው አባባል የኢትዮጵያ ብቸኛው ችግርና የችግር ምንጭ – ህወሃት -ይህንንም የህወሃትን ችግር ብቻውን ተጋፍጦና ታግሎ ለድል ያበቃው -ብቸኛው አብይና አመራሩ – ነው በማለት አዲስ ትርክታዊ አቀራረብ አስደምጠውናል፡፡ በእርግጥ በርካታ ሰዎች የጠ/ሚሩን ንግግር በከፍተኛ አድናቆት ሲገልጹት ተስተውሏል፡፡ ከእነዚህ አድናቂዎቻቸው ውስጥ በተለይም ለአማራው ህዝብ ህልውና እና ጥቅምና መብት የምንታገል ነን የሚሉ ፖለቲከኞችን፣ጋዜጠኞችንና አክትቪስቶችንም ተሳትፎን ማየትና መስማት ተችሏል፡፡ በእርግጥ የጠቅላይ ምኒስቲሩ ንግግር ለአድናቆት የሚበቃ ይዘትና አቀራረብ ያለው ስለመሆኑ ይህ ጸሃፊ ያምንበታል፡፡ በዚህ አድናቆት በተቸረው ንግግራቸው ውስጥ ይህ ጸሃፊ እንደ አንድ በእውነት በፋክት፣ባልተገደበ የተፈጥሮ መብት አማኝና አራማጅ ጋዜጠኝነቱና የታላቁ ብሄረ አማራ ተወላጅነቱና አፍቃሬ ኢትዮጵያዊነቱ የጠቅላይ ምኒስትሩን ንግግር ሾላ በደፈናው አይነት በአድናቆትና በጭብጨባ የሚያልፈው ሳይሆን መጠቀስና መገልጽ ሲገባቸው ስላልተገለጹት አማራዊ፣ሀገራዊና ስነ ማህበረሰባዊ ክስተቶችንና ችግሮችን በመጥቀስ ጠምሩን Challenge ማድረግን ይፈልጋልና- እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ 👉 በጠ/ሚሩ የተገለጹት 113 «ግጭቶች» ታሪክና ምንጮቻቸውን በተመለከተ፦ እንደ ዶ/ር አቢይ አህመድ የፓርላማ ውሎ አገላለጽ ከሆነ ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰቱ ብሄርና እምነት ተኮር ጥቃቶች ጭፍጨፋዎችን – እሳቸው አቃለው ግጭት ብለው የገለጹት -በሙሉ በህወሃት «ጁንታ» የተፈጸመ ነው ባይ ናቸው፡፡ እዚህጋ አንባቢ ሶስት ነጥባዊ ፋክቶችን ልብ እንዲል ይመከራል፦ 👉 1ኛ- 113 ግጭቶች ያሏቸውን 👉 2ኛ-ድንርጊቱን የፈጸመውና ያስፈጸመው የህወሃት ጁንታው ነው ያሉበትን ሁኔታ 👉 3ኛ-ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው ህወሃት ነው ብለው ያቀረቡበትን ሁኔታ ልብ ሊሉ ይገባል፡፡ ጠ/ምሩ በሁለቱ ዓመት ተኩል ውስጥ አንድም ግጭት በትግራይ ሳይካሄድ በሌሎች የሀገሪቱ ግዛቶች ውስጥ ተፈጽሟል ብለው በገለጹበት ዝርዝር ውስጥ በኦሮሚያ የግጭቶቹን ብዛት ከመግለጽ የዘለለ እንደ የአማራው ግጭትን መግለጫቸው የቅማንት የወልቃይት ወዘተ የግጭት መንስኤዎችን በገለጹበት ሁኔታ በኦሮሚያ የቄሮን የኦነግን እና የብልሹ ኦህዴዲያዊያንን ጸረ አማራዊና ጸረ ኢትዮጵያዊ ተግባርን ፈጽሞ ሳይገልጹና ሳያወሱ ነው ሆን ብለው ሸፋፍነው ለማለፍ የቻሉት፡፡ 👉 ለምንድነው በኦሮሚያ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የተጨፈጨፉት የአማራ ተወላጆች ሁኔታ ሊጠቀስ ያልተፈለገው??? 👉 ለምንድነው በኦሮሚያ ውስጥ ቁጥር አንድ ገዳይ የሆኑት ቄሮ ኦነግና የኦህዴድ ብልሹ ባለስልጣናት ሚና እና ተግባር በደፈናውና ጠቅለል ተደርጎ ሊገለጽ ያልተፈለገው?? 👉 ለምንድነው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ዛሬ ድረስ በየእለቱ በማንነታቸው አማራ ስለሆኑ ብቻ እየተጨፈጨፉ ስላሉት የአማራ ተወላጆች ጉዳይ ሊጠቀስ ያልተቻለው??? 👉 ለምንድነው ጠ/ሚሩ በቅርቡ በወለጋ ከ300 በላይ የአማራ ተወላጆች ለስብሰባ ተጠርተው የተጨፈጨፉበትን ጭፍጨፋ ሊጠቅሱ ያልደፈሩት??? 👉 ለምንድነው ጠ/ሚሩ የሀጫሉን ግድያ ጠቅሰው ሌሎች ታዋቂ ሰዎችም ኢላማ ተደርገው ነበር ብለው ሳለ እነዚህ ኢላማ ተደርገው ነበር ካሏቸው ውስጥ ሁለቱ አቶ እስክንድር ነጋና አቶ ልደቱ አያሌው ሆነው ሳለ መልሰው ደግሞ እነዚህን ሰዎች በማሰር እያሰቃዩ ያሉበትን ምክንያት ሊገልጹ ያልቻሉት??? 👉 ለምንድነው ጠ/ሚሩ 113ት ግጭቶች ከማለት ይልቅ ጥቃቶችና ጭፍጨፋዎች በማለት በትክክልና በግልጽ በማያሻማ ሁኔታ ለመግለጽ ያልደፈሩትና ያልፈለጉት??? 👉 ጠ/ሚሩ ለምንድነው ሁለት ዓመት ተኩል ይህንን ሁሉ (113 ጥቃቶችን) በመፈጸምና በማስፈጸም እጁ አለበት ያሉትን ህወሃት በጁንታ ስምና ውሱን ቡድንነት ብቻ ለመግለጽ የፈለጉት??? ይህ ውሱን ቡድን ብቻ ነውን ሀገሪቷንና በእሳቸው የሚመራውን መንግስት ቁም ስቅል ሲያሳይ የነበረው??? 👉 አጠቃላይ የኢትዮጵያን ችግር በአንድ በተሸነፈ ህወሃት ቡድን ላይ ደፍድፎ የኦነግን ቄሮን ስም ሳይጠቅሱ ዝም ማለት የሀገሪቷን ችግር ከመፍታት አኳያ ስርነቀል መፍትሄን ፈላጊነታቸውን ነው የሚያሳየው ወይንስ በግጭት ተጠቃሚነታቸው ስልትና አኳያ ኦነግንና ቄሮን ለቀሪው ግዜያቸው ፖለቲካዊ ትርፍ ሲሉ ያስቀመጧቸው መነገጃዎቻቸው ናቸው ??? ***የእውቅና ያለመስጠት ትርጓሜ ምንድነው ? 👉 የዶ/ር አቢይ አህመድ እውቅና ያለመስጠት ትርጓሜ ምንድነው??? ጠ/ሚሩ በተካሄደው ጦርነት በጣም በሚሰቀጥጥ ሁኔታ የኦሮሚያ ክልልን ልዩ ኃይል ያደረገውን ታላቅ ተጋድሎና ጦርነትን በይፋ እያወደሱ ሲገልጹ የአማራውን ክልል ምትክ የለሽ ተጋድሎና መስዋእትነትን ትንፍሽ ሳይሉ አልፈውታል፡፡ ጥያቄው ለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በየትኛው ግንባር ነው ተሰልፎ የተዋጋው ተብሎ የሚቀርበው ጥያቄ ሲሆን እንደ ጠ/ሚሩ አባባል የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በመሃል ሀገር ግንባር ከባድ ውጊያ ባያደርግ ኖሮ በመሀል ሀገር ያሉ የህወሃት አጋር ኤጀንቶች አጥለቅልቀውን ነበር ብለዋል፡፡ የእነዚህ ኤጀንት የተባሉትን ቡድኖች ስም ባይጠቅሱም ኦነግና ቄሮዎች መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ በጠ/ሚሩ እውቅና የተነፈገውና የተካደው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣የአማራ ክልል አርሶ አደር ሚሊሺያ፣የአማራው ተዋጊ ፋኖ ታላቅ ተጋድሎና መስዋእትነት የተካዱና እውቅና ያልተሰጣቸው ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ እውቅና ካልተሰጣቸው ውስጥ የአማራ መጨፍጨፍና ብሎም የብአዴኖቹ በተለይም የአቶ ገዱና የአቶ ደመቀን ታላቅ ተጋድሎና በዚህ ለውጥ ላይ ያላቸውን ይህ ቀረሽ እማይባል ሚናን እና ተጋድሎን በገደምዳሜ እንኳን ሳይገልጹ ሁሉንም እሳቸው ብቻ ታግለው ተጋድለው ህወሃትን እንዳሸነፉና ለውጡንም ለዚህ እንዳበቁ የገለጹበት መንገድ የለየለት ክህደትና ራስ ወዳድነት ሆኖ አይተነዋል፡፡ ጠ/ሚሩ የወታደራዊ ዘመቻውን በገለጹበት የጄኔራሎቹን ሚና እና አስተዋጽኦን በሚገልጽ ደረጃ ያቀረቡትን የቅጽል ስም አሰያየማዊ አቀራረብን ይህ ጸሃፊ በእጅጉ እያደነቀና ጠሚውን እያመሰገነ እኩል በአቻነትም የጠ/ሚሩን የተቀሩትን የአማራን ኃይሎችን ታላቅ ተጋድሎንና ተሳትፎን ያለመግለጻቸውን በእጅጉ እየኮነነ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ክህደት ነው ብሎ ለመግለጽ ይወዳል፡፡ አንድን የተፈጠረን ክስተት እንዳልተፈጠረ አድርጎ በዝምታ የማለፍ ትርጓሜ የእውቅና ለመስጠት ካለመፈለግ የሚመነጭ ሲሆን ይህም እውቅና ያለመስጠት ፍላጎት በሁለት የፍላጎት መንገድ የሚፈልቅ ነው፡፡ 1ኛ-የተፈጠረውን ክስተት ባለመፈለግና ባለመውደድ የሚፈጠር ሲሆን ፡፡ 2ኛ-የተፈጠረውን ክስተት ባለቤትና ዋና ተዋናይን ሚናን ባለመፈለግ የሚመጣ ነው፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው ብንል፦ ጠ/ሚሩ ወቅታዊ ክስተት የሆነውን የህወሃትን መሸነፍ በእጅጉ ይፈልጉና ይህንን ሽንፈት በማምጣት በኩል የአማራውን ተሳትፎንም የፈለጉ ሆነው ሳለ ግን የተፈለገው ተሳትፎ በጦር ግንባር በድብቅ መልክ እንጂ ሀገርና ህዝብ አውቆት መንግስት እውቅናን በይፋ ሊሰጠው በሚያስችል መልኩ እንዳይሆን አቢይ እንደፈለጉ እናያለን ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው መከላከያው በህወሃት ከበባ ስር በነበረበትና የአማራውን ተዋጊ ሚናን በመፈለጋቸው ብቅ ብለው በአደባባይ የአማራውን ተዋጊነትን በታላቅ አድናቆት ከገለጹና አጠቃላይ የአማራውን ሰፊ ህዝብ ሁለንተናዊ ሚናን ወደ ጦርነቱ ማዞር ከቻሉ በኃል በድሉ ማግስት በውጊያ ላይ ያልተሰለፈውን የኦሮሚያ ክልሉን ልዩ ኃይል ታላቅ ውጊያ እያሉ ሲገልጹ የአማራውን ተጋድሎ በጽጥታ ያለፉበት ዋና ምክንያት የአማራውን ጀግንነትና ተዋጊነት እንደፈሩትና እንዲወራም እንዲታወቅም እንዳልፈለጉ ያሳየናል፡፡ በነገራችን ላይ በተካሄደው ጦርነት የአማራው ተዋጊ ኃይል ያስመዘገበውን አንጸባራቂ ጀግንነትና ተጋድሎ በኦሮሚያ ክልሉ ልዩ ኃይልና በኦሮሚያ ተጣቂ ኃይሎች የተፈጸመ ሆኖ ቢሆን ኖሮ በሚነገረን እጅግ የተጋነነ ሽለላ ፉከራና ምስጋና ደንቁረንና ተጥለቅልቀን ነበር፡፡ እናም – የተፈጠሩ ክስተቶችን ስም ሳይጠቅሱ ማለፍ ማለት እውቅና አለመስጠት ሲሆን በዚህም መሰረት የኦነግና የቄሮ ጨፍጫፊነት፣የአማራውና የኦርቶዶክስ ተጨፍጫፊነትና የአማራ ልዩ ኃይል፣የአማራ አርሶ አደር ሚሊሺያና የአማራው ፋኖ ታላቅ ተጋድሎና መስዋእትነት በአቢይ መራሹ መንግስት በኩል እኩል ይፋ እውቅና የተነፈጉና እውቅና ሊሰጣቸው ያልተፈለጉ ክስተቶች መሆናቸውን ያየነውን ያህል በተጨማሪም የአቢይ አመራር በባልደረቦቹ የብአዴን አመራሮች በእነ አቶ ገዱና ደመቀ …ወዘተ በኩል የተካሄደውን ታላቅና ምትክ የለሽን ሚና እና ዛሬም እየተካሄደ ያለውን ታላቅ ምትክ የለሽ አስተዋጽኦን በይፋ ገልጾ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ያለመፈለጉን ፍላጎት እንዳለውም ያየንበት ሁኔታ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ እውቅና ያለመስጠት ማለት- ተመሳሳይና አቻ ጥቅማ ጥቅምና መብቶችንም ለመስጠት ፍቃደኛ ያለመሆን፤ ዝግጁ ያለመሆንና በአንጻሩም Sinister የሆነ Motive የተያዘ መሆኑን ያሳያል ማለት ነው፡፡ የእውቅና ያለመስጠት ትርጉም ይህ ብቻ ነው፡፡ 👉 መደምደሚያ- አቢይና አመራሩ እውቅና ሰጠ አልሰጠ ከግንዛቤ ሳናስገባ የአማራው ህዝብ ሚና በተለይም የብአዴን የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የአማራ አርሶ አደር ሚሊሺያና የፋኖው ሚና ምትክ የለሽ ታላቅ ስለመሆኑ ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል፡፡ በተለይም የብአዴን ምትክ የለሽ ሚናን የአቢይ አመራር ሆን ብሎ በማለባበስና በመሸፋፈን እንዳይታወቅ ቢያደርግም የራሱ ኦሮሞአዊው የኦህዴድ ፓርቲ ያልፈጸመውን ታላቅ ፖለቲካዊ ስራን የአማራው ብአዴን እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ እየበደለና እየጎዳ የአቢይ መራሹን መንግስት በሁለት እግሩ እንዲቆም በማስቻል ደረጃ የአንበሳውን ድርሻ እየተጫወተ ያለ ቡድን መሆኑን ማንኛውም አማራም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ ቢቀበለውም ባይቀበለውም ማወቅ ያለበት ሀቅ ነው፡፡ ይህ ማለት ይህ ጸሃፊ የብአዴን ደጋፊ ነው የሚል እድምታን ለመፍጠርና ለማሳየት ሳይሆን ጸሃፊው የብአዴን Critic ሆኖ ሳለ ይህ ሀቅ ግን ከጸሃፊው አቋም ጋር በተንሰላሰለ መልኩ የተገለጸ ሳይሆን ጸሃፊው በአቢይ መራሹ መንግስት ውስጥ ያለውን የኃይል አሰላለፍ በተጨባጭ ለመግለጽ በመፈለጉ የተገለጸ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡ አዎን-የብአዴንን ስራ መደገፍም ሆነ መቃወም ሌላ ሆኖ ሳለ ላለፉት ሁለት ተኩል ዓመታትና እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት በአቢይ መራሹ መንግስት ውስጥ የአብዴን ምትክ የለሽ ታላቅ ሚና እና ድርሻን መግለጽ ሌላ እውነታ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የአማራ ህዝብ በዚህ ጦርነት በልጆቹ በኩል ያደረገው አስተዋጽኦ የአቢይን መንግስት እውቅና በመፈለግ ሳይሆን በታሪክ ውስጥ ጠላት አድርጎት ዘርፈ ብዙ ጥቃት የከፈተበትን ህወሃትና ለመፋለምና ብሎም የተነጠቃቸውን እርስቶቹን ለማስመለስ ያደረገው ተጋድሎ ስለሆነ የአቢይን እውቅና ምስጋና እና አድናቆትን ፈልጎ ያደረገው ትግል አይደለም፡፡ እናም የዚህ ታላቅ ህዝብ ዋና አትኩሮትም የሚሆነው የታዋጋበትን ምክንያት እራሱ ለመመለስ በቀጣይ መንቀሳቀስን እንጂ አቢይ ፈቀደለኝ አልፈቀደልኝም እያለ እራሱን በራሱ እንዲያስር አይደለምና አቢይ እውቅና ባለመስጠቱ ፖለቲካዊ ኪሳራ የሚሰበስበው እራሱ አቢይ እንዲሆን ማድረግ እንጂ የአማራው ህዝብ ላደረገው ተጋድሎ የድንገቴ ክህደት ሊጋርደውና ሊደብቀው እንደማይገባ ህዝባችንን ጠንቅቆ ያውቃል፤ ብሎም ይሰራበታልም ብዬ እረዳለሁ፡፡ *** ይህን ጽሁፍ ያደረሱን የአማራ ሚዲያ ተከታታይ ናቸው። እርስዎም ሀሳብዎን ማጋራት ከፈለጉ በውስጥ ያድርሱን፡ አማራ ሚዲያ ማእከል የእርስዎ ድምጽ ነው!

Source: Link to the Post

Leave a Reply