በጀምስ ቦንድ የስለላ ፊልም የመጀመሪያዎቹ ሰባት ክፍሎች ዋና ተዋናይ የነበረው ሾን ኮነሪ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

በጀምስ ቦንድ የስለላ ፊልም የመጀመሪያዎቹ ሰባት ክፍሎች ዋና ተዋናይ የነበረው ሾን ኮነሪ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀምስ ቦንድ የስለላ ፊልም የመጀመሪያዎቹ ክፍሎች ላይ ዋና ተዋናይ የነበረው ሾን ኮነሪ በ90 ዓመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ሾን ኮነሪ በተወዳጁ የስላለ ፊልም ፤ የመጀመሪያውን ክፍል ጨምሮ በሰባት የጀምስ ቦንድ ፊልሞች ላይ ተውኗል።

አንጋፈው ተዋናይ በመኝታው ላይ እያለ ህይወቱ እንዳለፈ የተነገረ ሲሆን ለተወሰነ ጊዜ ጥሩ ጤንነት ላይ እንዳልነበረ ተነግሯል።

አስርት ዓመታትን በትወናት ላይ ያሳለፈው  ሾን ኮነሪ ፤  ባሳየው የትወና ብቃት የኦስካር ፣ ባፍታ እና ጎልደን ግሎብስ ሽልማቶችን  አግኝቷል።

ሾን ኮነሪ ከጀምስ ቦንድ ፊልም ባሻገር በኢንዲያና ጆንስ ፣ ዘ ክሩሴድ እና ዘ ሮክ የትወና ብቃቱን ያሳየባቸው ፊልሞች ናቸው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

The post በጀምስ ቦንድ የስለላ ፊልም የመጀመሪያዎቹ ሰባት ክፍሎች ዋና ተዋናይ የነበረው ሾን ኮነሪ ከዚህ አለም በሞት ተለየ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply