በጀርመን በርሊን ከተማ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተደረገ ያለውን የለየለት ዘረኛ አገዛዝን እና አፈናን የሚያወግዝ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት…

በጀርመን በርሊን ከተማ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተደረገ ያለውን የለየለት ዘረኛ አገዛዝን እና አፈናን የሚያወግዝ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በ ጀርመን በርሊን ከተማ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተደረገ ያለውን የለየለት ዘረኛ አገዛዝን እና አፈናን የሚያወግዝ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ግንቦት 26/2014 ዓ/ም ተካሂዷል። በጀርመን ሰዓት አቆጣጠር ከ12 ሰዓት እስከ 15 ሰዓት በበርሊን ቤተ መንግስት ፊት ለፊት በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ አካላት ተሳትፈዋል። የተቃውሞ ሰልፉን በዋናነት የአማራ ማህበራት የጋራ ግብረ ኃይል በጀርመን ያዘጋጀው መሆኑ ተገልጧል። በፋኖ እና በአጠቃላይ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ግድያ፣አፋና እና እስርን በሚያወግዘው ሰልፍም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ነጮችም ጭምር ተገኝተው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። በሰልፉ ከተላለፉት በርካታ መልዕክቶች መካከል:_ 1) በኢትዮጵያ በአማራ ላይ የሚፈጸመው ማንነት ተኮር መንግስታዊ ጥቃት ይቁም፤ 2) በህግ ማስከበር ስም በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የአማራ ፋኖዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶችና ሌሎች ንጹሃን አማራዎች በአስቸኳይ ይለቀቁ፤ 3) ፋኖ የአማራ ህዝብ ብሎም የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት ነውና በመንግስት ትጥቅ ለማስፈታት፣ለመከፋፈልና ለመበተን የተከፈተበት መንግስታዊ ጥቃት ይቁም፤ አንድ ፋኖ፣ አንድ አማራ!፣ በራሱ ስንቅና በራሱ ትጥቅ ለሀገሩና ለወገኑ ታላቅ መስዋዕትነት ለከፈለው ለአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ይህ የጥቃት ዘመቻ አይገባውም! 4) በወልቃይት፣ጠገዴ እና በራያ አሸባሪው ትሕነግ የፈጸመውን የዘር ፍጅት አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ድርጅትና ሌሎች የሰብአዊነት ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት እንዲመረምሩትም መልዕክት አስተላልፈዋል። 5) በእምነቶች መካከል መንግስታዊ ጣልቃ ገብነት ይቁም፤ ለመከፋፈልና ለማጋጨት የሚደረግን እንቅስቃሴ እናወግዛለን። እዚህ ላይ በሰላማዊ ሰልፉ ተገኝተው መልዕክት ካስተላለፉት መካከል በሰብአዊ መብት ዙሪያ ትኩረት አድርጋ የምትሰራው ሙሉጣይ ክብረት (ሀያት መሀመድ) መገኘቷን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አረጋግጧል። አሚማ ከሙሉጣይ ክብረት (ሀያት መሀመድ) ጋር ካደረገው ቆይታ እንደተረዳው:_ በዘር እና በሀይማኖት የምትከፋፍሉን ወገኖች እጃችሁን አንሱልን እኛ አንድ ነን፣ አንከፋፈልም የሚል ጥብቅ መልዕክት አስተላልፋለች። አሸባሪዎች በአማራ እና አፋር የፈጸሙትን ወረራ ተከትሎ ተደፍረው በቤታቸው ውስጥ በከፍተኛ ስቃይ የሚገኙ ወገኖች በአስቸኳይ የህክምና እርዳታ እንዲሰጣቸውም ጠይቃለች። ይህንን አስከፊ ወንጀል የፈጸሙ አካላት ለህግ ቀርበው እና ህጋዊ ቅጣት ያገኙ ዘንድም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሚዲያ ተቋማትና የፍትህ አካላት በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርባለች። 6) በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል እና በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ላይ የሚፈጸመው ግድያ፣መፈናቀልና መሳደድ ይቁም፤ 7) የአብይ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ ክህደት ፈጽሟል! ተረኝነት ይቁም! የአብይ አገዛዝ የትሕነግ አገዛዝ ባለአደራ ነው። 8 ለሆዳችሁ ያደራችሁ ምስለኔዎች ወደ ህዝባችሁ ተመለሱ የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችም በሰልፉ ላይ ተላልፈዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply