በጀርመን የሸዋሮቢትና አካባቢው የበጎ አድራጎት ማህበር ከሸዋ የሰላም እና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) ጋር በመተባበር የአልትራሳውንድ መሳሪያዎችን ለ4 የጤና ተቋማት ድጋፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ…

በጀርመን የሸዋሮቢትና አካባቢው የበጎ አድራጎት ማህበር ከሸዋ የሰላም እና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) ጋር በመተባበር የአልትራሳውንድ መሳሪያዎችን ለ4 የጤና ተቋማት ድጋፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጀርመን የሸዋሮቢትና አካባቢው የበጎ አድራጎት ማህበር ከሸዋ የሰላም እና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) ጋር በመተባበር የአልትራሳውንድ መሳሪያዎችን ለ4 የጤና ተቋማት ድጋፍ ማድረጋቸውን የሸዋሰማ ስራ አስኪሂያጅ ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው አስታውቀዋል። ግምታቸው 23,633 ዩሮ ማለትም 1,315,410.16 ብር የሆኑ 4 የአልትራሳውንድ (Ultrasound) የህክምና መሳሪያዎችን ነው ለ4 ሆስፒታሎች ታህሳስ 23 ቀን 2014 ማበርከታቸው የተገለጸው። 1ኛ) ለየካቲት 12 ሆስፒታል፣ 2ኛ) ለለእናት ሆስፒታል አለም ከተማ/መርሀቤቴ 3ኛ) ለደብረ ብርሀን ሆስፒታል ደብረብርሀን እና 4ኛ) ለዘውዲቱ ሆስፒታል ወረኢሉ በዛሬው እለት ድጋፍ አድርገናል ብለዋል ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፡፡ በጀርመን የሸዋሮቢትና አካባቢው የበጎ አድራጎት ማህበር ሊቀመንበር አቶ ሸዋንግዛው ሙላቱ እንዲሁም የሃፈንሆ ከተማ ምስጋና እንደሚገባቸው ተገልጧል፡፡ 75% ትራንስፖርት ድጋፍ ላደረገው Engagement Global እና ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ ድጋፍ ላደረጉ በጀርመን የኢትዮጵያ ኢንባሲ፤ ለጉምሩክ ኮሚሽን እና ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል፡፡ ሸዋ ሰላም እና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) ለአካባቢው እና ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን የተለያዩ እና በርካታ በጎ ተግባራትን በማከናወን ላይ የሚገኝ የሲቪክ አደረጃጀት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply