
ባለፈው ቅዳሜ በጀርመኗ ጊሰን ከተማ በተከሰተው ረብሻ ተሳትፈዋል በተባሉ 125 ኤርትራውያን ላይ የወንጀል ክስ መመስረቱን የአገሪቱ ፖሊስ ገለጸ። ሰኔ 01/2015 ዓ.ም. ቅዳሜ በጊሰን ከተማ ከኤርትራ የባሕል ፌስቲቫል ዝግጅት ጋር ተያይዞ በተፈጠው ሁከት በርካታ የጀርመን ፖሊስ አባላት ላይ እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። ይህ በኤርትራውያን አማካይነት የተከሰተው ሁከት በከተመዋ ውስጥ ስጋትን ፈጥሮ የነበረ ሲሆን፣ የጀርመን ፖለቲከኞችን እና ባለሥልጣናትን አስቆጥቷል።
Source: Link to the Post