በጀብ መንጋ ምክንያት መጠጥ ቤቶች እስከ ምሽት 12 ሰአት ብቻ እንዲሰሩ ተወሰነ፡፡በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲዮ ዞን በዲላ እና አካባቢው የጅብ መንጋ ህዝቡን ወጥቶ እንዳይገባ ስጋት ፍጥሯል…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/P0CdCAvE-90OQ0TtaET7XpcW9R7l9WvZRr4_gc4pWXO_7zVqUaBJWGiK-W2CYqIGU10276PxGJ_O0uy4ZVSP3xKbEUu6wS8uYAR0KMUZOfI7C4DRCfM2qOhm_6xZMZeL3E_HUjEYHZpteCYaGc_ysOp9M5oFVcWbKBOIQlc_6oTfVVWO3wOZ0sswXHoPIvFofclwyTkTEQ1xvoQ8fLKGwoTmitzW4bU7FLQIeqVucSs8GQ3Az-TCQsBuntEzKmMC527gxPDL74f321fMylj2IeX4sh6rpw42PSo7OtZMCUXTbDGzB904U1S8sJk4gjboM13gDVY2pw7KRezfErhlgw.jpg

በጀብ መንጋ ምክንያት መጠጥ ቤቶች እስከ ምሽት 12 ሰአት ብቻ እንዲሰሩ ተወሰነ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲዮ ዞን በዲላ እና አካባቢው የጅብ መንጋ ህዝቡን ወጥቶ እንዳይገባ ስጋት ፍጥሯል ተባለ፡፡

በዲላ ዙሪያ በሚገኙ ወረዳዎች ባሉ አከባቢዎች የጅብ መንጋ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ተከትሎ ህብረተሰቡ ለመጠበቅ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ናቸው ተብሏል፡፡

የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ አለማዬሁ ጎበና የተባሉ ግለሰብ ግንቦት 11/2016 ዓ/ም አምሽተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ በጅብ መንጋ መበላታቸውን ፖሊስ ገልጻል፡፡

የዲላ ከተማ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር መሰለ ወንዱ እንደተናገሩት አቶ አለማየሁ ወደ ቤት ሳይመለሱ በመቅረቱ ቤተሰቦች ፍለጋ በወጡበት ወቅት በመንገድ ላይ ልብስ ጫማና የተለያዩ የሰውነት ክፍል የቀሩ ስጋና አጥንት ማግኘታቸው ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ምርመራና ባገኙው ምልክቶች ግለሰቡ በጅብ መበላታቸውን መረጋገጡን የገለጹት አዛዡ በአከባቢው ከፍተኛ የጅብ ጩሄት እንደነበረ ከአከባቢው ማህበረሰብ ማረጋገጥ መቻሉን አስታውቋል፡፡

የጅብ መንጋ እንቅስቃሴ ስጋት በመጨመሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በጊዜ ወደየ ቤታቸው መግባት እንደለበትና ልጆች የቤት እንስሳትን ስጠብቅ ጥንቃቄ እንድያደርጉና ወደ ጫካ ውስጥ እንዳይሄዱ አሳስቧል።

በአካባቢው ለረዥም ጊዜያት ጅብ እንደነበሩ የገልጹት ም/ኢ/ር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በአጎራባች ቀበሌያት መሠል ጥቃት መድረሱን በማንሳት ማህበረሰቡ በጊዜ በመግባት የሚሰጠዉን የጥንቃቄ መልእክት በአግባቡ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply