በጁንታው መወገድ ዋነኛ ተጠቃሚ የሚሆነው  የትግራይ ህዝብ ነው – አቶ አሻድሊ ሃሰን

በጁንታው መወገድ ዋነኛ ተጠቃሚ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ ነው – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መቐለ መሽጎ በነበረው የህወሓት ጁንታ መወገድ ዋነኛ ተጠቃሚ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የሃገር መከላከያ ሠራዊት መቐለን በመቆጣጠሩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ይህንኑ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ህወሓት ለ27 ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጦ እርስ በእርስ ሲያጋጭ ነበር ብለዋል።

ይህን ለማሳካት የሀገሪቱን ሕዝቦች በብሄር በመከፋፈልና ግጭት በመቀስቀስ ስልጣኑን ለማስቀጠል ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ እንዲፈጠር ማድጉን አመላክተዋል።

በጠረፍ አካባቢ የሚገኙ ክልሎችን ደግሞ በሞግዚት በማስተዳደር የተፈጥሮ ሃብታቸውን መዝረፉን ያስረዱት አቶ አሻድሊ፥ ክልሎች በአግባቡ እንዳይለሙም አድርጓልም ነው ያሉት።

ህወሓት በትጥቅ ትግል ያካበተውን ሴራ ለውጡን ለማደናቀፍ እንደተጠቀመበት አመልክተው በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች ንጹሃን እንዲጎዱና ንብረት እንዲወድም አድርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

The post በጁንታው መወገድ ዋነኛ ተጠቃሚ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ ነው – አቶ አሻድሊ ሃሰን appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply