You are currently viewing በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት አማራዎችን ትጥቅ ማስፈታትና ማሳደዳቸውን እንደቀጠሉበት ነው፤ ገበያ ላይ የነበሩ 4 አማራዎችን አፍነው ወስደዋል። አማራ…

በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት አማራዎችን ትጥቅ ማስፈታትና ማሳደዳቸውን እንደቀጠሉበት ነው፤ ገበያ ላይ የነበሩ 4 አማራዎችን አፍነው ወስደዋል። አማራ…

በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት አማራዎችን ትጥቅ ማስፈታትና ማሳደዳቸውን እንደቀጠሉበት ነው፤ ገበያ ላይ የነበሩ 4 አማራዎችን አፍነው ወስደዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት አማራዎችን ትጥቅ ማስፈታትና ማሳደዳቸውን እንደቀጠሉበት መሆኑ ተገልጧል። ለገበያ የሄዱ አማራዎች ጭምር እየተሳደዱ ነው፤ 4 አማራዎችን አፍነው መውሰዳቸው ተሰምቷል። አምስተኛው አርሶ አደር የጸዳው አለምነው ላለመያዝ ሲሸሽ ተከታታይ ጥይት የተተኮሰበት ቢሆንም መትረፉ ታውቋል። አማራዎቹ የካቲት 12 ቀን 2014 ደርጌ ኮቲቻ ከተባለው ቀበሌ ወደ ጃርዴጋ ከተማ ለገበያ በመጡበት ወቅት ነው አፈናው የተፈጸመባቸው። የካቲ 12 ቀን 2014 የታሰሩ የአማራ አርሶ አደሮች:_ 1) መንግስቴ አያሌው፣ 2) ጌጡ አስናቀ፣ 3) መከረ አያሌው እና 4) ተስፋዬ ገሰሰ እንደሚባሉ ታውቋል። በተመሳሳይ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ቂልጡ ጬካ ቀበሌ ስብሰባ የጠራው የፌደራል ፖሊስ ሼህ ኑርዬ የተባሉ የ60 ዓመት አዛውንትን አስሮ ወደ ጃርዴጋ ካምፕ መውሰዱ ታውቋል። ከሰሞኑ በተከታታይ ቀናት በርካቶች መታሰራቸውና ትጥቅ የተወሰደባቸው መሆኑን አሚማ መዘገቡ ይታወሳል። ከቀናት በፊት የታሰረው የ1 ዓመት ከ6 ወር ህጻን ከእነ አያቱ የካቲት 13/2014 መፈታቱ ተሰምቷል። በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታሰሩ አማራዎች በእስር ላይ ባሉ ኦነጎች ያለጠያቂ በር ተዘግቶ ክፉኛ እንደሚሰቃዩ ስለሚያውቁ በጥይት መሞትን ይመርጣሉ ሲሉ ብዙዎች ይናገራሉ። በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ካሉ 24 ቀበሌዎች መካከል ደርጌ ኮቲቻ እና ቂልጡ ጬካ ብቻ አሁንም ድረስ በአማራ ሚሊሾች ተከብረው እንደሚገኙ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply