በጃፓን በተከሰተዉ ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 48 ደረሰ፡፡ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ በኢሺካዋ ግዛት በአንድ ሌሊት ብቻ ወደ 45ሺህ የሚጠጉ ቤቶች የመብራት አገልግሎታቸዉ ተቋርጧል፡፡…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/BUwUbHpQPFP51p8N7M-e72SUqvoSvJecns1Njm6pvTOh2OH9NY2smgPmfQ8HxuPTyDyBUiU8vq3SH_8xiaNNezbA6-_hQW-u4HKSPzbytdI2pkB2c6gW8Apks0H2X8YlpuCsnq8ihdjA0cpEOOl3UjCyhVCKXQwGL7_36mzn1MMHbhVby9bWifQb9Vq_MkQvzXlNF-6hGG2LbQOzB1Y9qwTxktU_GEJh9fMT01nI7Aiq246Dssu5rAUaWq04SQi5BOPi5NvLTs65iaUk-DVhvWBqmdQp74qvTsZoI0ld36uSqog7zaTg4mlSwmIWy0twHgn9ME-wcep1a8OkOSfSSw.jpg

በጃፓን በተከሰተዉ ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 48 ደረሰ፡፡

ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ በኢሺካዋ ግዛት በአንድ ሌሊት ብቻ ወደ 45ሺህ የሚጠጉ ቤቶች የመብራት አገልግሎታቸዉ ተቋርጧል፡፡

62ሺህ ዜጎች ቦታዉን ለቀዉ እንዲወጡ የታዘዘ ሲሆን፤ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ 1ሺህ ወታደሮቻቸዉን ወደ ቦታዉ መላካቸዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በዋጂማ ከተማ በተመዘገበዉ የ1.2 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ዉጪ መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡

በአገሪቱ በደረሰዉ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አማካይነት ሱናሚ ሊከሰት ይችላል በማለት ተጥለዉ የነበሩ ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ በዛሬዉ ዕለት መነሳታቸዉም ተዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply