በጃፓን ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ መጨመር ለሃገሪቱ ስጋትን ፈጥሯል።ይህ ዜና በአለም ሶስተኛውና ትልቁ የኢኮኖሚ መገኛ ለሆነችው ጃፓን መጥፎ ዜና ሆኗል።የድፍድፍ ዘይት እና የ…

በጃፓን ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ መጨመር ለሃገሪቱ ስጋትን ፈጥሯል።

ይህ ዜና በአለም ሶስተኛውና ትልቁ የኢኮኖሚ መገኛ ለሆነችው ጃፓን መጥፎ ዜና ሆኗል።

የድፍድፍ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ፣ ወደ ጃፓን የሚላኩ እቃዎች ዋጋ 34 በመቶ ጨምሯል ተብሏል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዋጋ ግሽበቱ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች መጠንን 0.9% እንዲቀንስ አድርጎታል።

በጃፓን ከውጭ በሚገቡ ምርቶች በኩል እየተከሰተ ያለው ውድነት በተለይ ከሞላ ጎደል የኃይል ፍጆታዋን ከውጭ በሚላኩ ዕቃዎች ላይ ጥገኛ ላደረገችው ለሃገረ ጃፓን እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ።

ለጃፓን ሸማቾችም ፣ ደሞዛቸው ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ሁኔታው ተባብሷል ሲል ብልምበርግ ዘግቧል።

ከጦርነቱ በኋላም ቢሆን በተለያዩ ዋጋዎች ላይ ተጨማሪ የሚጣሉ እገዳዎች አዝማሚያ እየባሰ እንደሚሄድ ዘገባው ጠቁሟል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ጃፓን ለድርጅቶች እና ለህዝቦቿ ከፍተኛ ወጪዎችን በመመደብ ወደ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አዝቅት ልታመራ ትችላለች ነዉ የተባለዉ።

የዓለም ሶስተኛዋ የኢኮኖሚ ባለቤት ጃፓን በሩብ ዓመት ውስጥ ኢኮኖሚዋ ወደ ውድቀት ሊያመራ እንደሚችል የምጣኔ ሃብት እያስጠነቀቁ ነው።

ጃፓን አሁን ላይ ከአሜሪካ የምታስገባቸው ምርቶች ዋጋ 39 በመቶ ጨምሮባታል ነዉ የተባለዉ።

ብሉምበርግ

በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply