በጅሩ እና በመርሃቤቴ ፋኖዎች በጥምረት ወገቡን የተመታዉ የጠላት ሀይል እንደለመደዉ ህዝብን በአረመኔነት ማሰቃዬቱን ቀጥሏል —————— በሸዋ በሞረትና ጅሩ ወረዳ በቀን…

በጅሩ እና በመርሃቤቴ ፋኖዎች በጥምረት ወገቡን የተመታዉ የጠላት ሀይል እንደለመደዉ ህዝብን በአረመኔነት ማሰቃዬቱን ቀጥሏል —————— በሸዋ በሞረትና ጅሩ ወረዳ በቀን 12/6/2016 ግፈኛው የአቢይ አህመድ ኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊት አማራን ለማጥፋት በተሰጠው ተልኮ መሰረት ባንዳ ሚኒሻ እና ፖሊስ በማስቀደም በፋኖ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ አድርጓል:: ሆኖም የማይቀመሱት የጀግናው የራስ አበበ አረጋይ ልጆች እንዲሁም ከመርሀቤቴ እና ከጅሩ ቁርጠኛ ፋኖዎች በጥምረት ቀድመው የደፈጣ ቦታ በመያዝ ባንዶችን እና የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊትን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከብርሀን ብልጭታ በፈጠነ ኦፕሬሽ የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊትን ከእነ ባንዶቹ በታትነዉታል:: በፋኖዎች የተሸነፈዉ ባንዳ እና የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊት በብስጭት በእነዋሪ ከተማ ሲቪል ነዋሪዎችን እያንገላታ: እየገረፈ እንዲሁም እየገደለ አምሽቷል:: እንደተለመደዉም ፍጹም የሆነ አረመኔአዊ ስራዎችን በህዝብ ላይ እያከናወነ ይገኛል::ህጻናትና ሴቶችን በመግደል: ያልታጠቁ ሲቪሎችን በመረሸን: ባለትዳሮችን በመድፈር እና ሽማግሌዎችን በመግደል ስራ ላይ ተጠምዷል::ይሄ አረመኔአዊ አካሂዱም በህዝብ ዘንድ ጥርስ እንዲነከስበት እና እንዲተፋ ሁኔታዎችን ያፋጥናቸዋል እንጂ ህዝባዊዉን ትግል ፈጽሞ የሚቀለብሰዉ አይሆንም::ፋኖም በህዝብ ላይ የደረሰዉን ግፍ በመበቀል የህዝብን እንባ ያብሳል:: ==== የመረጃ ምንጭ:- የራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ ናደው ሻለቃ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ ምኒልክ ማንደፍሮ

Source: Link to the Post

Leave a Reply