በጅቡቲ ሙቀት ኢትዮጵያውያን ሾፌሮች ሕይወታቸው አለፈ

ሁለት ኢትዮጵያውያን ሾፌሮች እና አንድ የመኪና ጠጋኝ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጅቡቲ በተከሰተው ከባድ ሙቀት ሰበብ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

ሌሎች ሁለት ደግሞ ሙቀቱ ባስከተለባቸው የጤና ችግር ሆስፒታል ውስጥ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ሲል አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

እስከ 50 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በደረሰው ሙቀት ለሳምንታት ያለ ስራ የተቀመጡ ሾፌሮች አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሁኔታ አሳሳቢ ነው ሲል የኢትዮጵያ የከባድ መኪና ሾፌሮች ማኅበር አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply