
በጅግጅጋ ከተማ በተከሰተው የእሳት አደጋ 932 ሱቆች ወድመዋል፤ በከተማዋ አዲሱ ታይዋን ተብሎ የሚጠራው የገበያ ማዕከል በተከሰተው አደጋ ወድሟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 1/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በጆግጅጋ ከተማ ሰኔ 30/2015 ከምሽቱ 5:00 ገደማ ባጋጠው የእሳት አደጋ በከተማዋ ትልቁ ገበያ በተለምዶ አዲሱ ታይዋን ተብሎ የሚታወቀው የገበያ ማዕከል ወድሟል። የእሳት አደጋው በሰዎች እና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ፣የእሳት ቃጠሎው መንስኤ እና እስካሁን ያደረሰው ኪሳራ እየተጣራ ይገኛል ተብሏል። ለ5 ሰዓታት የቆየውን የእሳት አደጋው በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን በስፍራው 932 ሱቆች በእሳቱ ወድመዋል፤ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መገባቱንም የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አብዲቃድር ረሺድ ተናግረዋል። የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እንዲሁም የኢፌዲሪና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቃጠሎው ያደረሰውን ጉዳት ቦታው ድረስ በመሄድ ተመልክተዋል ተብሏል። መረጃው_የሶማሊ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ነው።
Source: Link to the Post