በገበታ ለሀገር ሦስት ፕሮጀክት ያሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

በገበታ ለሀገር ሦስት ፕሮጀክት ያሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በገበታ ለሀገር ሦስት ፕሮጀክት ማለትም በኮይሻ፣በጎርጎራ እና በወንጪ በቀረቡ ዲዛይን ስራዎች ላይ ያለበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑባቸው ክልሎች ርእሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሮጀክቶቹ ቀደም ብለው መገምገም እንደነበረባቸው ጠቅሰው በወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት ሊዘገይ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ስራው ተጀምሮ እስከሚያልቅ የፌደራል መንግስት የፕሮጀክቶችን የግንባታ ሂደት ይከታተላልም ነው ያሉት፡፡

ወደፊት ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁም ለክልሎች እንደሚያስረክብም ነው የገለጹት፡፡

ክልሎቹም ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገውን በጀት ለማሟላት ህዝቡን ማሳተፍ እንደሚገባቸው ተነስቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቶቹ የአካባቢውን ባህላዊ እና ተፈጥሯዊ እሴቶች በጠበቀ መልኩ እንደሚከናወኑም አውስተዋል፡፡

በሰላማዊት ካሳ

The post በገበታ ለሀገር ሦስት ፕሮጀክት ያሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply