በገና በዓል ሊያጋጥም የሚችለውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለአሐዱ እንደተናገሩት በመጪው የገና በዓል ሊያጋጥም የሚችለውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር በሶስት ፈረቃ የተከፋፈሉ የአደጋ ሰራተኞች ዝግጁ መደረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከህዳር 18 ቀን እስከ ጥር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ያለውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት አድረጓል ያሉት አቶ ጉልላት 30 የሚሆኑ የአደጋ መቆጣጠሪያ ተሸከርካሪዎችን፤ 19 አምቡላንሶችን፤ 2 ቦቲዎችን፤ 6 ኮማንድ ካሬዎችና 2 ክሬኖች አደጋ ቢያጋጥም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥም የሚችለውን የእሳት አደጋ ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን፤ መብራት ሃይልና ከከተማ ፖሊስ ጋር የተቀናጀ ስራ እየሰራ ስለመሆኑ አስታውቋል፡፡

*********************************************************************************

ቀን 27/04/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

ምስል፡- የእሳት ቃጠሎ

Source: Link to the Post

Leave a Reply