በገንዳ ውሃ ከተማ አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ በፀጥታ አካላት መገደሉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ…

በገንዳ ውሃ ከተማ አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ በፀጥታ አካላት መገደሉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

በገንዳ ውሃ ከተማ አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ በፀጥታ አካላት መገደሉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰደው ተማሪ ሙላለም አደራጀው ካፒታል ከጓደኞቹ ጋር የሽኝት ፕሮግራም አምሽቶ ሲመለስ ፓትሮል ሲያደርጉ ነበሩ በተባሉ የፀረ ሽምቅ አባላት በጥይት መገደሉን ነዋሪዎች ገልፀዋል። ግድያው የተፈፀመው በገንዳ ውሃ ከተማ ቀበሌ 01 ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ በግምት ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ መሆኑ ተገልጧል። መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናቸውን በማጠናቀቅ ፎርም ከሞሉ በኋላ ትናንት መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት የነበራቸውን የሽኝት ፕሮግራም አጠናቀው ሲመለሱ ነው ተማሪው የተገደለው የሚሉት ምንጮች በአካሉ ላይ በአፈሙዝ ድብደባ ተፈፅሞበታል፤ በጥይት ከቆሰለ በኋላም ወደ መተማ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ለማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል። ነዋሪነቱ በገንዳ ውሃ ከተማ አርማጭሆ ሰፈር የሆነው ተማሪ ሙላለም የተገደለው ወደ ጣቢያ ለመሄድ ባለመፍቀዱ እና መሳሪያ ለመንጠቅ ሙከራ በማድረጉ ነው የሚሉ አሉ። ስለጉዳዩ ያነጋገርናቸው አንድ የገንዳ ውሃ ነዋሪ ህጻን ልጅ በመሆኑ ጦር መሳሪያ ለመንጠቅ ሙከራ አያደርግም፤ ይልቁንስ ፀረ ሽምቆቹ ከልክ ያለፈ ኃይል በመጠቀም የፈፀሙት ግድያ ነው፤ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚደረግ ከንቱ ጥረትም ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል። እንደተባለው እንኳ ቢሆን ተማሪውን ከመግደል ሌላ መፍትሄ መፈለግ ሲችሉ አልመው መግደላቸው ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲሉም አክለዋል። የተፈፀመው ግድያ ነውረኛና አሳዛኝ ነው ሲሉ የገለፁት ነዋሪዎቹ መረጃ ማጣረሱን ትተው ገዳዩን አጣርተው በህግ እንዲጠየቁ እንፈልጋለን ብለዋል። ሌላ የተደበደበና የታሰረ ተማሪ ስለመኖሩም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በተመሳሳይ ማስረሻ የተባለ የገንዳ ውሃ ወጣትም ትናንት መጋቢት 5 ቀን 2013 በርሃ ላይ ከብቶችን እየጠበቀ ሳለ ከመንግስት የፀጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት መገደሉም ተገልጧል። ስለተፈፀመው ግድያ መረጃ እንዲሰጡን በሚል ለገንዳ ውሃ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ለኢንስፔክተር አብራራው የደወልን ቢሆንም “እስኪ ቆዩ” በማለት ስልካቸውን ዘግተዋል። በተጨማሪም የአስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊው አቶ አስፋው ከተማ የተጣራ መረጃ ለመስጠት ከ30 ደቂቃ በኋላ እንድንደውል ቀጠሮ ያሲያዙን ቢሆንም፤ በቀጠሮአችን ስንደውል ስብሰባ ላይ ነኝ በማለት መረጃ ለመስጠት አልተባበሩንም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply