በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ሩፋኤል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል፡፡አደጋዉ የተከሰተዉ በአንድ የቢሮ እቃዎች ማምረቻ መጋዘን ዉስጥ መሆኑም ታዉቋል፡፡በአሁኑ ሰዓት የእሳትና ድንገተኛ አ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/SeKIMYZk0sNFJuiGb-prp-iDutEq9ufTzMhXp8WrDBRTuEz3cVmA_TXhSQKVrxBw60xuoETGXl20wWokUfJAdPyxfGPFE2P8yASIYugxaWYwBekjdhLo1cM1hI0eifo-P6Dwc1cTWbytgYhXB_v9binaK_ubvnc-eSR9esbcrK2zLnY-SMlAD0NYFpn2emRchxIOHKwlFyiNk2y_9M7z7XQKFJBj2WOeuooUoXuRLmdnWocUixg4xz8FxwlN3yage39QJNrmBqCGyA_Nbjp5NQ5geRrI7U_mVSHTjvNtHti3Ik_htssQGM6BgBGMq7V0w3aiN4hBprJfYjwUSSO-qQ.jpg

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ሩፋኤል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል፡፡

አደጋዉ የተከሰተዉ በአንድ የቢሮ እቃዎች ማምረቻ መጋዘን ዉስጥ መሆኑም ታዉቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞችና 13 ተሸከርካሪዎች በቦታዉ ላይ የደረሱ ሲሆን፣ እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ በአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረዉናል፡፡

አካበባዉ በርካታ ቤቶች በተጨናነቀ መልኩ ተሰርተዉ የሚገኙበት በመሆኑ እሳቱን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንዳደረገዉም ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

ከቀኑ 6፡30 አካባቢ በተከሰተዉ በዚህ የእሳት አደጋ እስካሁን ባለዉ መረጃ የተወሰኑ ሰዎች በጭስ የመታፈን አደጋ አጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡
አሁን ላይ የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ገና ጥረት እየተደረገ ሲሆን ቀሪ መረጃዎችን እንደደረሱን የምናቀርብላችሁ ይሆናል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply