
በጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የአድዋ ድል መሃንዲስ የሆነውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክ ምስል ያለበት፣ አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ያለበት እንዲሁም ሌሎች ተዛማች ልብሶችን የሚሸጡ ሱቆች እየታሸጉ መሆኑ ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የአድዋ ድል መሃንዲስ የሆነውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክ ምስል ያለበት፣ አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ያለበት እንዲሁም ሌሎች ተዛማች ልብሶች የሚሸጡ ሱቆች ከሰሞኑ እየተለዩ በመታሸግ ላይ ስለመሆናቸው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር በሚከተለው መልኩ አጋርቷል:_ ወይ አዲስ አበባ… የግፍ ግፍ‼ በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የሚገኙ የሀገር ባህል ልብስ መሸጫ ሱቆች በበላይ አካል ትዕዛዝ እየታሸጉ ነው። የፊታችን የካቲት 23 የጥቁሮች ታላቅ የድል የሆነው የአድዋ በዓልን ለማክበር አዲስ አበቤ በታላቅ ጉጉት ላይ ይገኛል። ይሁን እንጅ የድሉ መሃንዲስ የሆነውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክ ምስል ያለበት፣ አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ያለበት እንዲሁም ሌሎች ተዛማች ልብሶች የሚሸጡ ሱቆች ናቸው እየተለዩ ከሰሞኑን መዘጋት የጀመሩት። በሽሮ ሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎች እና አዲስ አበቤዎች ላይ ይህ ድርጊት ታላቅ ቁጣ ፈጥሯል። ይሄን እኩይ ድርጊት እየፈፀሙ ካሉ አካላት ውስጥ አንዱ አቶ ፀጋዬ ደበሌ ይባላል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ነው። በሸሮ ሜዳ እና አካባቢው ባሉ ሱቁች ላይ እርምጃ እየወሰደ የሚገኝው ይህ ባለጊዜ ሰውዬ እንደሆነ ታማኝ ምንጮች መረጃውን አድርሰውኛል። ይህ ግለሰብ በኦርቶዶክስ ተዋህዳ እምነት ተከታይ የሆኑ የጉለሌ የመንግስት ሰራተኞችን አሳስሯል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ 3 የሚጠጉ አመራሮችን የሲኖዶሱ ፎቶ በሞባይል እስኪሪን ላይ አድርጋችኋል በሚል እንዲታሰሩና ከኃላፊነታቸው እንዲታገዱ አድርጎል።
Source: Link to the Post