በጉማይዴ ሕዝብ ግጭት የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ቀጥተኛና ድብቅ ተሳትፎ እንዳለበት በነዋሪዎች ተገለፀ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 06/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በደቡብ…

በጉማይዴ ሕዝብ ግጭት የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ቀጥተኛና ድብቅ ተሳትፎ እንዳለበት በነዋሪዎች ተገለፀ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 06/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በደቡብ ክልል የጉማይዴ ሕዝብ ላይ ከ2011 ዓም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው ጥቃት ቀጥሏል። የደቡብ ክልል ከምስረታው ሲጀምር የጉማይዴ ወረዳን በማፍረስ ነበር በቀጠናው አዲስ ካርታ የሰራው። ይህ ነሐሴ 1987 ዓ/ም የዘር ፖለቲካ አቀንቃኙ የሕወሓት ህገመንግስት መጽደቁን ተከትሎ በጉማይዴ የተፈጸመ ግፍ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ማፍረስ ስራው የሆነው ይሄው ደቡብ ክልል ጉማይዴን ማዕከል አድርጎ በ2003 ዓ/ም 5 ወረዳዎችን (ኮንሶ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ኧለ እና ዲራሼ) አንድ ላይ አቅፎ የተቋቋመውን የሰገን አከባቢ ሕዝቦች ዞን መጣ የተባለው ጠንቀኛው ለውጥ በመጣ ማግስት 2011 ዓ/ም ላይ አፈረሰው። የሚሉት የጉማይዴ ነዋሪዎች ዛሬም በከፍተኛ ውጥረት ያልተረጋጋ ሰላም ውስጥ ይገኛሉ። ባለፉት ዓመታት የዞኑን መፍረስ ተከትሎ አሁንም የጉማይዴ ከተማ የሆነውን የሰገን ከተማ አስተዳደር እንዲፈርስ ተደረገ። በተደጋጋሚ የመዋቅር መፍረስ የጉማይዴን ሕዝብ ስላስቆጣው የጉማይዴ ሕዝብ #የጉማይዴ_ልዩ_ወረዳ ጥያቄ ለክልሉ መንግስት አቀረበ። ይህንን ጥያቄ በመቃወም በ2011 ዓም የመንስት አካላት ባስነሱት ግጭት ቡንቲ በተባለ ቦታ ላይ አማራና ኮሬ ብሔረሰብ እንዲጋጩ አድርገው ሁለቱም ሕዝብ ቤትና ንብረታቸው በእሳት በመውደሙ ተፈናቅለው እስከ ዛሬም እንደተበታተኑ ይገኛሉ። ያንጊዜ የጀመረው ግጭት እስካሁን 5 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ሌሎች አካባቢዎችም ሰው አልባ ሆነዋል፣ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከ250 በላይ ንፁሃን ሞተዋል፣ አካል ጉዳት የደረሰባቸውን ቤት ይቁጠራቸው። የጉማይዴ ሕዝብ በኮንሶና በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በቀጥተኛና ድብቅ ተሳትፎ እየተገደለ ያለው በወያኔ የዘር ፖለቲካ አልደራጅም ሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ነን ቀድሞ የፈረሰው የጉማይዴ ወረዳ ይመለስልኝ በማለቱ ብቻ ነው። በጉማይዴ ውስጥ አማርኛና ኦሮምኛ መግባቢያ ቋንቋ ናቸው። በተጨማሪነት ኮንስኛ፣ ቡርጂኛ፣ ዲራሽኛ፣ ጋሙኛ፣ ኮይርኛ፣ ከተማው ላይ የሚነገሩ ቋንቋዎች ናቸው። የጉማይዴ ሕዝብ ዛሬ በቁጥር ከ200 የሚበልጥ ሰው ከ6 ወር ጀምሮ እስከ 3 አመት ድረስ በኮንሶ ካራት ከተማ ደረቅ ጣቢያ በእስር እየማቀቁ ናቸው። ከመጋቢት 19-30/2014 የሆነው ይህ ነው አርሶአደሩ ከቤቱ እንዲወጣ በሶስት ቀበሌ ላይ በሌሊት ኮንሲታ በተባለው ታጣቂ ቡድን ተኩስ ተከፈተ፣ ሰገንገነት፣ ዱጋያና መልሰ ቀበሌያት ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው ወጡ። ቤታቸው ሙሉበሙሉ ተዘረፈ፣ የቤታቸው ቆርቆሮ ተነቅሎ ወደ ኮንሶ ተጫነ፣ የቀረው በእሳት መጋየት ጀመረ፣ ሕዝቡ በከተማ ላይ ተቀምጦ በዝምታ ለሚመለከተው ለደቡብ ክልል ልዩ ሀይልና ፌደራል ፖሊስ አመለከተ፣ ይሁን እንጂ ጥቃቱ አሁንም አልቆመም፣ የመለጋ ማርያም ቤተክርስቲያን በር ተሰብሮ ንብረት መዝረፍ ተጀመረ… በዚህን ጊዜ ሕዝቡ ዝም ብሎ መመልከት ባለመቻሉ ተቆጣና እራሱን ወደ መከላከል ገባ። በመጋቢት 21/2014 የተጀመረው ውጊያ ያለማንም ሀይባይ እስከ 30 ድረስ ቀጠለ። ከ30 በኋላ ቆሟል ማለት ሳይሆን መግደሉንና ማውደሙን ደክመው ነው የተውት። የሰገን ዙሪያ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ሥር ካልዋሉ ነገም ሰው መግደልና ቤተክርስቲያን ማስወደማቸው አይቀርም። በዚህ መጋቢት ማለቂያ ላይ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፣ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ሀላፊ ጉዳዩን በዝምታ በመመልከት የሰገን ዙሪያ ወረዳ የብልፅግና አመራሮች ሙሉበሙሉ የተሳተፉበት ጦርነት በጉማይዴ ሕዝብ ላይ በርካታ ኪሳራ አድርሶ አልፏል፣ ዛሬም በቦታው የፀጥታ ስጋት በመኖሩ ተፈናቃዮች ያለጠያቂ ፀሐይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ይገኛል። #ስንታየሁ ቸኮል ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply