You are currently viewing በጉራጌ የወልቂጤ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አደባባይ ወጥተው አቀባበል እንዲያደርጉ ቢጎተጉቱም አልተሳካም ተባለ። መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አቶ…

በጉራጌ የወልቂጤ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አደባባይ ወጥተው አቀባበል እንዲያደርጉ ቢጎተጉቱም አልተሳካም ተባለ። መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አቶ…

በጉራጌ የወልቂጤ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አደባባይ ወጥተው አቀባበል እንዲያደርጉ ቢጎተጉቱም አልተሳካም ተባለ። መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አቶ ታረቀኝ ድጋፌ በፎቶ አስደግፎ እንዳጋራው ካድሪዎች የጸጥታ አካላትን በየቤቱ በር በማሰማራት ህዝቡ እንዲወጣ እየተማጸኑ ነው። Tarekegn Degife በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገጹ ይህን አጋርቷል:_ “ውጡ ? አንወጣም!” አጀብ እኮ ነው! ፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ሃይል_ በር እያንኳኳ ጠቅላዩ መጥቷል ውጡ? በር የተንኳኳባቸው ሰዎች_ አንወጣም ! ከገጠር ህዝቡን በአምቡላንስ እየጫኑ ለማምጣት እየሞከሩ ነው! ካድሬው ድራማው ይጋለጥብኛል፤ የታፈነው ህዝብ የዝምታ ጩኸት ይሰማብኛል ብሎ ተደናብሯል ! አብይ አህመድ በሁለት ሂሊኮፍተር ወልቂጤ ስታዲዮም የደረሰ ቢሆንም 100 ካድሬዎች እና ከፊል የካድሬ ቤተሰብ አቀባበል አድርጎለታል። በካድሬው እቅድ መሰረት እነ አብይ አህመድ ከወልቂጤ ገስታውስ ቁርስ በልተው ወደ አዳራሽ ከክላስተራዊያን ካድሬዎች ይወያያሉ። በጣም አስገራሚ ነገሩ የፀጥታ ሃይሎች ከገብርኤል ቤተክርስቲያ አስቀድስው ሲመለሱ የነበሩ ነጭ ነጥላ የለበሱ እናቶችን በማገት “አብይ አህመድን አሸብሽባችሁ ተቀብሉ” ቢባሉም፣ መንገደኛውም ሆነ ከቤተስኪያን ተመለሽ መዕምናን “አንቀበልም።” ብለው ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው ገብተዋል። ወልቂጤ ፀጥ ረጭ ብሏል። ህዝቡም በዝምታ ቤቱ እያሳለፈ ነው። የአዳራሹ ጭብጨባ እና እንቶ ፍንቶ ወሬ ተመልሰን የምናየው ይሆናል! ለማስታወስ ጠሚ አብይ አህመድ ከአራት ዓመታት በፊት ወደ ወልቂጤ በመጣ ሰዓት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማው ህዝብ ወጥቶ ተቀብሎታል። ዛሬ ደግሞ 100 ካድሬ ብቻ። ካድሬውም አምኖበት አይደለም። እታሰራለሁ፣ ከስልጣን እነሳለሁ፣ እሰደዳለሁ ብሎ እንጂ። መቋጫው አብረን የምናየው ነው! “በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ እንዴት ያ ሁሉ ህዝብ ሸሸ?” የአብይ ጥያቄ መሆን አለበት የጉራጌ ትግል ግን በሰላማዊ መንግድ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ከወልቂጤ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply