በጉራ ፋርዳ ለተፈጸመው ጥቃት የዞኑና የወረዳው አመራሮች አስተባባሪዎች መሆናቸው ተሰማ። /// ሰአሻራ ሚዲያ ጥቅምት 14/2013 ዓ.ም ባህር ዳር ///….

በጉራ ፋርዳ ለተፈጸመው ጥቃት የዞኑና የወረዳው አመራሮች አስተባባሪዎች መሆናቸው ተሰማ። /// ሰአሻራ ሚዲያ ጥቅምት 14/2013 ዓ.ም ባህር ዳር ///… በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ በግፍ የተገደሉ የአማራ ማህበረሰብ አባላት ቁጥር አስካሁን በውል ተለይቶ አልታወቀም፡፡ ምንጫችን ከቦታው እንደገለጸልን እስከ ትናንት ድረስ የሟቾች ቁጥር ከሰላሳ ስምንት በላይ መድረሱን ገልጾልን ነበር፡፡ በዞኑ ለተፈተማ ፅቃጽ የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፤ የጉራ ፋርዳራዳ ወረዳ አመራሮችና ቀበሌ አመራሮች የቀጥታ ተሳታፊዎች ናቸው ሲሉ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልጸውልናል፡፡ ምንጫችን እንደገለጹልን ከሁለት ወራት በላይ የተዋቀረ እና የተደራጀ ስልጠና ከብሄረሰቡ ለተውጣጡ አባላት ሲሰጥ እንደነበር እና አማራን ከቦታው የማስወጣት እቅድ ይዘው የጦር መሳሪያን በድብቅ በማስገባት ጥቃት ሊፈትሙ ችሏል ብሏል፡፡ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎችም እስካሁን ድረስ በጫካ ውስጥ መሽገው እንደሚገኙ ገልጸውልናል፡፡ የሟቾች ቁጥርም ከሰላሳ ዘጠኝ መብለጡን ምንጫችን ገልጸውልናል፡፡ ክቡራን የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮች ከምንጫችን ጋር ያደረግነው የስልክ ቆይታ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ ዘጋቢ ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply