በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ

በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በእርምጃው 17 የኦነግ ሸኔ አባላት መቁሰላቸውን እና የቡድኑ 13 አባላት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልፀዋል።
እርምጃው የተወሰደው የፀጥታ አካላት እና ህብረተሰቡ በጥምረት በሰሩት ስራ እንደሆነ መናገራቸውን ከኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከአጥፊው ህወሓት ቡድን ተላላኪዎች በተለያዩ አካካባዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ ተልዕኮ ወስደው በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን ደግሞ የጉጂ ዞን የፀጥታና አስተዳዳር ቢሮ ኃላፊ አቶ ዋሌ ዱንጎ ተናግረዋል።
የዞኑ የፀጥታ አካላት በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች እስካሁን ባደረጉት ፍተሻ ከአጥፊው ህወሓት ቡድን ተልዕኮ ወስደው ጥፋት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሶስት ግለሰቦች ከ100 ሺህ ብር ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።
የጉጂ ዞን አስተዳደሪ አቶ ታደለ ኡዶ፥ የዞኑ ነዋሪዎች በዞኑ ለሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች ጥበቃ እና እንክብካቤ በማድረግ ለሀገሪቱ ልማት እድገት የሚሰሩትን ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

The post በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply