You are currently viewing በጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በገዳዮች ተከበዉ አሁንም ድጋፍን ለሚጠይቁ ዜጎች መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸዉ እና የህግ ከለላ እንዲደረግላቸዉ ሲል የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም…

በጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በገዳዮች ተከበዉ አሁንም ድጋፍን ለሚጠይቁ ዜጎች መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸዉ እና የህግ ከለላ እንዲደረግላቸዉ ሲል የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም…

በጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በገዳዮች ተከበዉ አሁንም ድጋፍን ለሚጠይቁ ዜጎች መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸዉ እና የህግ ከለላ እንዲደረግላቸዉ ሲል የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ጥሪ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በወለጋ በሰዎች ላይ ስለደረሰዉ አስቃቂ ግድያ የተሰጠ መግለጫ:_ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሃገራችን የተደረገዉን የለዉጥ ሂደት ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢዎች ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊቆም ባለመቻሉ አሁንም ከሞት መርዶ ልንወጣ አልቻልንም። በተለይም በኦሮሚያ ክልል በወለጋ አካባቢዎች ካሁን በፊት በተደጋጋሚ ለተፈፀመዉ ብሄርንና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ም/ቤታችን ሲያወግዝ መቆየቱ የሚታወስ ነዉ። ይሁንና ሰሞኑን በወለጋ ዞን በጊቢ ወረዳ በቶሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች በጽንፈኛ ኃይሎች ብሄርንና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈፀመዉ አሳዛኝ አሰቃቂ የጀምላ ግድያ የበርካታ ሰዎች ህይዎት መጥፋቱና በመስጂዶች የተጠለሉት ጭምር የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸዉን ከአካባቢዉ ህ/ተስብና በተለያዩ ሚዲያዎች እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ስለሆነም:_ 1) ይህን አሰቃቂ ጥቃት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በጥብቅ የምናወግዘዉ እና በደረሰዉ ጥቃት ከልብ ያዘንን መሆኑን እያስታወቅን መንግስት በተደጋጋሚ የሚደርሰዉን ጥቃት እንዲያስቆምና ወንጀለኞች በግልጽ ለህግ እንዲቀርቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን። 2/ በአካባቢዉ በገዳዮች ተከበዉ አሁንም የመንግስትን ድጋፍ ለሚጠይቁ ዜጎች መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸዉ እና የህግ ከለላ እንዲደረግላቸዉ እንጠይቃለን። 3/ ዜጎች በብሄርና በሃይማኖት ጥቃት ሳይደርስባቸዉ በየትኛዉም የአገሪቱ ክፍል በሰላም ሰርተዉ ሃብት አፍርተዉ እንዲኖሩ መንግስት የህዝቦችን ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አጥብቀን እንጠይቃለን። 4/ ካሁን በፊትም ሆነ አሁን በተፈጠረዉ ጥቃት ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ወገኖች አስፈላጊዉ ድጋፍና ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ አበክረን እንጠይቃለን ብሏል የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply