You are currently viewing በጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ጽንፈኛ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያን የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ቁስለኞች በየጫካው ወድቀው እየተገኙ ነው፤ ህክምና ለማግኘት አለመቻላቸው ነገሩን አሳሳቢ አድርጎ…

በጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ጽንፈኛ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያን የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ቁስለኞች በየጫካው ወድቀው እየተገኙ ነው፤ ህክምና ለማግኘት አለመቻላቸው ነገሩን አሳሳቢ አድርጎ…

በጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ጽንፈኛ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያን የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ቁስለኞች በየጫካው ወድቀው እየተገኙ ነው፤ ህክምና ለማግኘት አለመቻላቸው ነገሩን አሳሳቢ አድርጎታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ በሶስት አካባቢዎች በተለይም ከህዳር 19 ቀን 2014 ጀምሮ ግልጽ ጦርነት የከፈቱት ጽንፈኛ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያን ብዙ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል። ጸረ አማራው እና ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ አፈጣጠር ያለው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ፣የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹና ከህዝብ ደመወዝ የሚከፈላቸው የመንግስት አካላት ጭምር በአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ አሊ ሚካኤል፣ ጠጋጊጊ እና ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ28 በላይ አማራዎች ተገድለዋል። በተጨማሪም በርካቶች ቆስለዋል፤ ሀብት ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ተቃጥሏል፤ ሰብላቸውን እንዳይሰበስቡ ተከልክለዋል፤ ሽህዎች ተፈናቅለዋል። ህዳር 22 ቀን 2014 የአማራ ሚሊሻዎች በየጫካው ባደረጉት ፍተሻ 5 የአማራ እና የኦሮሞ ቁስለኞችን ወድቀው አግኝተዋል፤ ከመካከላቸው እጃቸውና እግራቸው ክፉኛ የተጎዱ ሁለት ህጻናት ይገኙበታል። ለህክምና እንዲደርሱ ተሽከርካሪ ቢጠየቅም ምላሽ የሚሰጥ የመስተዳድር አካል አልተገኘም ተብሏል። በህክምና እጦት ሊሞቱ ነው! ህዳር 22 ቀን 2014 ረፋድ ላይ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የትሕነግ ደጋፊዎች በጊዳ መንደር 4 ሊያልፉ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊትና ሚሊሾች ላይ ተኩስ ከፍተው ሲመልሷቸውም ተገቢ የአጸፋ ምላሽ እንዳይሰጥም ከምስራቅ ወለጋ ዞን ተከልክሏል የሚል ቅሬታ ለአሚማ ደርሷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply