በጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና አጋሮቹ በሰላማዊ አማራዎች ላይ የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከጥቃቱ እየሸሹ የነበሩ ሰዎች በውሃ ሙላት ተወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

በጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና አጋሮቹ በሰላማዊ አማራዎች ላይ የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከጥቃቱ እየሸሹ የነበሩ ሰዎች በውሃ ሙላት ተወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና አጋሮቹ በሰላማዊ አማራዎች ላይ የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከጥቃቱ እየሸሹ የነበሩ ሰዎች በውሃ ሙላት መወሰዳቸውን የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ተናግረዋል። አንገር ጉትን ላይ ያለው መከላከያ ሰራዊት እስከ ጊዳ አያና መንደር 3 ድረስ አጅቦ የሸኛቸው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት እና አጋሮቻቸው ህዳር 27/2015 ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 8 ሰዓት በቡድን መሳሪያ በመታገዝ በፈጸሙት አሰቃቂ ጥቃት ከ70 በላይ አማራዎች በግፍ ተገድለዋል፤ በርካቶች ቆስለዋል፤ ሽህዎች ተፈናቅለው በጫካ ገብተዋል። በግፍ ከተገደሉት መካከልም:_ 1) አባሆይ አለሙ ዘገዬ (የአንዶዴ ስላሴ መነኩሴ) 2) አለማዬሁ አዳሙ፣_አንዶዴ ስላሴ የተቀበሩ ሲሆን 3) ሀብታሙ ሲሳይ እና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን ሀብታሙ መለከታ ሚካኤል የተቀበረ መሆኑ ተገልጧል። ይህን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና የኦነግ ሸኔ እንዲሁም የአካባቢው የጸጥታ አካላት የፈጸሙትን የጅምላ ፍጅት ተከትሎ በርካቶች ከጥቃቱ ለማምለጥ ሲሸሹ አንገር በተባለ ወንዝ ሙላት መወሰዳቸው ተሰምቷል። ህዳር 27/2015 እና ህዳር 28/2015 በአንገር ወንዝ ሙላት ከተወሰዱት መካከልም:_ 1) በላይነህ፣ 2) በለጠ፣ 3) ጌቶ እና 4) ገደፍ የተባሉ አማራዎች ይገኙበታል። አቶ ገደፍ የተባሉ አባት ከገጠር እህል ለማስፈጨት ሻሾ በር በመጡበት አንዶዴ ስላሴ አካባቢ እያሉ በጥይት ተመተው በመቁሰላቸው ለህክምና በሚል ወደ ቱሉጋና በአልጋ ተሸክመው እየወሰዷቸው ሳለ አንገር በተባለው ወንዝ ሙላት መወሰዳቸው ተሰምቷል። በተኩሱ ምክንያት ከአንዴዲ ዲቾ ወደ ቱሉጋና ተሻግረው ካደሩ በኋላ ለቀብር ህዳር 28/2015 እየተመለሱ ከነበሩት መካከልም በላይነህ፣በለጠ እና ጌቶ የተባሉ የአንዶዴ ዲቾ ነዋሪዎች ይገኙበታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply