You are currently viewing በጊዳ አያና ወረዳ ኦሚ አንሳራ በሚባል ቀበሌ 3 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በግፍ ተገደሉ፤ እንዳይቀበሩም ክልከላ ተጥሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም…

በጊዳ አያና ወረዳ ኦሚ አንሳራ በሚባል ቀበሌ 3 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በግፍ ተገደሉ፤ እንዳይቀበሩም ክልከላ ተጥሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም…

በጊዳ አያና ወረዳ ኦሚ አንሳራ በሚባል ቀበሌ 3 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በግፍ ተገደሉ፤ እንዳይቀበሩም ክልከላ ተጥሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ኦሚ አንሳራ በሚባል ቀበሌ 3 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በግፍ ተገድለዋል። እድሜያቸው ከ40 እስከ 45 የሚሆኑ እነዚህ አባዎራዎች ከኦሮሞ ጋር ተጋብተው የተዋለዱ በመሆናቸው የሚነካችሁ የለም፤ ከአሁን በኋላ እናንተ ኦሮሞ ሆናችኋል በሚል ካዘናጉ በኋላ ነው በመኖሪያ ቤታቸው አፍነው በስለት በማረድ የገደሏቸው ተብሏል። አሰቃቂው ግድያ የተፈጸመው የካቲት 15 ቀን 2014 በጠራራ ጸሀይ መሆኑ ተገልጧል። ወንድማማቾችን:_ 1) አሰፋ ደመላሽ አበበ፣ 2) ደሱ ደመላሽ አበበና የአጎታቸውልጅ 3) ይርጋ ገረመው አበበን በአሰቃቂ መልኩ በስለት ገድለዋቸዋል። አስከሬናቸው እንዳይቀበርም በወራሪ ቡድኑ ክልከላ ተጥሏል። በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚኖሩ አማራዎች በማንነታቸው የተነሳ መውጫ መግቢያ አጥተው ለከፋ ረሃብ እና ለሁለንተናዊ ችግር ተጋልጠው የሰሚ ያለህ እያሉ መጮህ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply