በጋምቤላ ሸማቂዎች ለሰላማዊ ትግል ትጥቅ አወረዱ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-6c76-08db429618fd_tv_w800_h450.jpg

ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር(ጋነግ) ብሎ የሚጠራው ቡድን አመራር፣ የትጥቅ ትግሉን በመተው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማካሔድ መወሰኑን፣ 196 የቡድኑን አባላት ይዞ፣ ትላንት ጋምቤላ መግባቱን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

የጋነግ ጦር መሪ ጋትሉዋክ ቡም ፓል፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከነታጣቂዎቻቸው ትጥቅ አውርደው መግባታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

አቶ ጋትሉዋክ፣ ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ ከሚጠራው የሸማቂ ቡድን ጋራ ያላቸውን ግንኙነትም ማቋረጣቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply