”በጋምቤላ በጎርፍ ሳቢያ የተፈናቀሉ ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ናቸው” ዩ ኤን ኦቻ

https://gdb.voanews.com/80470000-c0a8-0242-7141-08dab6d3bdb4_tv_w800_h450.jpg

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥእንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታውቋል ።

 እየተደረገላቸው  ያለው ድጋፍም ተመጣጣኝ አይደለም ብሏል።

 ካለፈው አመት ነሐሴ ጀምሮ እስከአሁኑ ጥቅምት ወር የጣለው ዝናብባስከተለው ጎርፍ በጋምቤላ ክልል ከሚገኙ 12 ወረዳዎች ውስጥ ከ185 ሺ በላይየሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውንም ጽ/ቤቱ ትናንት ባወጣው ሪፖርትአመልክቷል።

የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት በበኩሉ ተፈናቃዮችወደየአካባቢያቸው እየተመለሱ ነው ብሏል።

የተመለሱትን ሰዎች ቁጥር ግን  አልጠቀሰም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply