በጋምቤላ ከተማ ተጥሎ የቆየዉ የሰዓት እላፊ ተነሳ

ዕረቡ ሐምሌ 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የጣለውን የሰዓት እላፊ ገደብ ማንሳቱን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤቱ በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት፤ በከተማው የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን በመለየት ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 ድረስ የሰዓት ገደብ ተግባራዊ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህም መሠረት ጽ/ቤቱ ከአንቡላንስና ከፀጥታ ሀይል ተሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት መሆኑን ገልጾ ነበር።

ቢሆንም ግን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሰሞኑን በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከቀናት በፊት ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ መነሳቱን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply