You are currently viewing በጋምቤላ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ሲል ኢሰመጉ በሪፖርቱ አመላከተ፡፡  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀምሌ 1…

በጋምቤላ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ሲል ኢሰመጉ በሪፖርቱ አመላከተ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 1…

በጋምቤላ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ሲል ኢሰመጉ በሪፖርቱ አመላከተ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 15/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ግንቦት 3 ቀን 205 ዓ.ም በሁለት ቀበሌዎች ውስጥ ባሉ የአኝዋ እና የንዌር ጎሳዎች መካከል ሲሆን ግጭቱ የጀመረው እና እየተስፋፋ የሄደው በዋናነት ሁለቱ ጎሳዎች በሚገናኙበት ኢታንግ ልዩ ወረዳ ውስጥ ባሉ ቀበሌዎች እና በጋምቤላ ከተማ ነው ብሏል፡፡ በኑዌር እና በአኝዋ ጎሳዎች መካከል በተደጋጋሚ ጊዜ የጎሳ ግጭቶች የሚነሱ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተወሰኑ መሻሻሎች ታይተው የነበረ ቢሆንም ይህ ግጭት ዳግም ተቀስቅሷል ነው ያለው፡፡ ይህ የጎሳ ግጭት በጋምቤላ ከልል በተለይም በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በስፋት የነበረ በመሆኑ ምክንያት በእነዚህ አካባቢዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት እና መፈናቀል ስለመድረሱ በሪፖርቱ አካቷል። በኢታንግ ልዩ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን እና በወረዳው ባሉ የተለያዩ ግጭቱ ከፍተኛ በነበረባቸው ቀበሌዎች ላይ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ኢሰሙ ከአካባቢዎቹ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን አስታውቋል፡፡ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ገና ቀበሌ ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በጥቃቱ ምክንያት የተግደሉ ሰዎች አስክሬኖች እንዳልተነሱ፣ በእዚህ የጎሳ ግጭት ላይ የተለያዩ መሳሪያዎችን የታጠቁ ሰዎች እየተሳተፉበት በመሆኑ የጉዳቱን መጠን ከፍተኛ አድርጎታል ብሏል። በአኝዋ ዞን ጎማ ወረደ ፑኝዶ ወረዳ አሁን ላይ የተሻለ የጸጥታ ሁኔታ ቢኖርም በአካባቢው በተደጋጋሚ ተመሳሳይ የጎሳ ግጨቶች ስለሚነሱ ስጋቶች መኖራቸውን አንዲሁም ይህንን ግጭት ለመቆጣጠር የክልሉ መንግስት በአጠቃላይ ከልሉ ላይ ተፈጻሚ የሚሆነ ሰዓት እላፊ ማወጁንና የክልሉ ፖሊስ፤ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት ግጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ስለመሆኑ ጠቁሟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply