በጋምቤላ ክልል ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም እስከ ጥር ወር 2016 ዓ.ም በተለያዩ ወቅቶች ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 113 ሰዎች የአካል ጉዳት ማጋጠሙን ኢሰመኮ አስታወቀ፡፡የኢ…

በጋምቤላ ክልል ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም እስከ ጥር ወር 2016 ዓ.ም በተለያዩ ወቅቶች ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 113 ሰዎች የአካል ጉዳት ማጋጠሙን ኢሰመኮ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 138 ሰዎች ህይወት አልፏል ብሏል፡፡

በሪፖርቱ እንደተመለከተው ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም በኢታንግ ልዩ ወረዳ ሥር በሚገኝ ፒኝዋ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አንድ ግለሰብ መጥፋታቸውን ተከትሎ፣ በፒኝዋ ቀበሌ እና አጎራባች በሆነው በሌር ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት በወቅቱ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የግለሰቦች እና የተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት እና ዘረፋ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በነበሩ ግጭቶች እና ጥቃቶችም በክልሉ የተለያዩ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ላይ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንዲሁም ከመጠለያ ጣቢያ ውጪ ለምግብ ፍለጋ እና ለተለያዩ ጉዳዮች ሲንቀሳቀሱ በታጠቁ ቡድኖች እና ግለሰቦች በደረሰ ጥቃት ብዙ ሰዎች መገደላቸውን እና የአካል ጉዳት መድረሱን ሪፖርቱ አካቷል፡፡

በዚሁ ግጭት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በጎግ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ እና ጋምቤላ ከተማ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም እስከ ጥር ወር 2016 ዓ.ም በተለያዩ ወቅቶች በሰዎች ሕይወት እና በንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ማድርሱን በላከው መግለጫ መመልከት ይቻላል፡፡

ኢሰመኮ ማረጋገጥ በቻለው መረጃዎች እና ማስረጃዎች መሠረት ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ 113 ሰዎች ላይ አካል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም በግለሰቦች እና ተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በሪፖርቱ በዝርዝር ተካቷል፡፡

በክልሉ መንግሥት የተጀመሩ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራዎች እንዲቀጥሉ እና በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ ሊደረግ እንደሚገባ ኮሚሽኑ በሪፖርቱ አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply