በጋቦን ባለሥልጣናት መኖሪያ ቤቶች ጥሬ ገዘብ የታጨቀባቸው በርካታ ቦርሳዎች ተገኙ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-ce6f-08dbaae94483_w800_h450.jpg

በተለያዩ የጋቦን ባለሥልጣናት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጥሬ ገንዘብ የታጨቀባቸው በርካታ ቦርሳና የእጅ ሻንጣዎች መገኘታቸውን ጋቦን 24 የተሰኘው የመንግሥት ቴሌቪዥን ትናንት ሐሙስ አሳይቷል።

ይህ የተከሰተው ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎን ከሥልጣን ያስወገዱት ወታደራዊ መሪዎች ሙሰኞች ናቸው ያሏቸውን የቀደሞ ባለሥልጣናት ለመወንጀል እየቀሰቀሱ ባሉበት ወቅት መሆኑ ተመልክቷል፡።

ወታደራዊ መሪዎቹ ከአደገኛ እጾች ዝውውር ጀምሮ በተለያዩ ክሶች ተጠያቂ ያደረጓቸውን በርካታ የቦንጎ ካባኔ አባላትን ከትናንት በስቲያ ረቡዕ አስረዋል።

ከታሳሪዎቹ መካከል የቦንጎ ልጅ ኑሪደን ቦንጎ ቫለንቲን እና የቀድሞ ካቢኔ ድሬክተር እንደሚገኙበት ተነግሯል።

ተጠቃሾቹ የተያዙት ከተያዘው ገንዘብ ጋር በተገናኘ ስለመሆኑ ግን ግልጽ አለመሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply