በጋዛ ህጻናት በረሃብ እየሞቱ እንደሆነ ዶ/ር ቴድሮስ ተናገሩ፡፡

በሰሜናዊ ጋዛ ህጻናት በረሃብ እየሞቱ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስታውቀዋል።

እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ከጥቅምት በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝቱን በአልአውዳ እና በከማል አድዋን ሆስፒታሎች ማድረጉንም ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በሆስፒታሎቹ ቅዳሜና እሁድ ባደረገውም ጉብኝት ሁኔታው “አሳዛኝ እና አስከፊ” ሆነውም እንዳገኟቸው ዶ/ር ቴድሮስ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አጋርተዋል።

በምግብ እጦት ምክንያት አስር ህጻናት እንደሞቱ ገልጸው ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ተከስቷልም ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply