በጋዛ የሟቾች ቁጥር ወደ 38ሺህ መጠጋቱ ተገለጸ፡፡እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለችዉን ጦርነት ተከትሎ ተጨማሪ 43 ሰዎች በመገደላቸዉ የሟቾች ቁጥር ከ37ሺህ 9መቶ በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/lCjAkAjka8ygYHwhNhB07s09B7Xdhl8d0pxDhcq23IaKQqJvjh0PJ9jQMznbMf88iC2RBKnV4rDydPA5MHCPV2xqvDd2c405KOUqfrY8DQB4bxsqLoc88Lcq--fs-f7sJonkJDj0YX_yeHJB8ldlsGPCcpUW-8f9YFWIDA4LGk91zxTKr3FsCH1h5idzdXTZN3s7UzNidG96t134_4qpb7u2_aZYTCbMBdgUjnJcZF2tLDiWiQwjUKUcXTxXSxmq0xBOyLdpBxftH0RWlOZvTIy2HmD5yQpOK18ohkRgc8eLU0NzTvFE5cPlkvZeUV4ayPgIig3XaVvBzhoh-ZvY6A.jpg

በጋዛ የሟቾች ቁጥር ወደ 38ሺህ መጠጋቱ ተገለጸ፡፡

እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለችዉን ጦርነት ተከትሎ ተጨማሪ 43 ሰዎች በመገደላቸዉ የሟቾች ቁጥር ከ37ሺህ 9መቶ በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገዉ 86ሺህ9መቶ69 ሰዎች በጦርነቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

እስራኤል በቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ በፈጸመችዉ ጥቃት 43 ሰዎች ሲገደሉ 1መቶ 11 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸዉም ነዉ ሚኒስቴሩ የገለጸዉ፡፡

አሁንም ድረስ በፍርስራሹ ስር ብዙዎች መኖራቸዉ የተገለጸ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም ሊያስወጧቸዉ እንዳልቻሉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ከ8 ወራት በላይ ባስቆጠረዉ ጦርነት ጋዛ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይራለች የተባለ ሲሆን የምግብ፣ የንጹህ ዉሃ እና የመድሃኒት አቅርቦት ወደ ስፍራዉ መግባት እንዳይችል ሆኗል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply