You are currently viewing በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና አቤቱታ ላይ ዐቃቢ ህግ አስተዬቱን ይዞ ባለመቅረቡ በይደር ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ፤ ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ህዳር 1/2015 የ…

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና አቤቱታ ላይ ዐቃቢ ህግ አስተዬቱን ይዞ ባለመቅረቡ በይደር ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ፤ ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ህዳር 1/2015 የ…

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና አቤቱታ ላይ ዐቃቢ ህግ አስተዬቱን ይዞ ባለመቅረቡ በይደር ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ፤ ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ህዳር 1/2015 የዐቃቢ ህግን ምላሽ እና የተከሳሽን አቤቱታ በመመልከት ውሳኔ እንደሚሰጥ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከግንቦት 19/2014 ጀምሮ ላለፉት 5 ወራት ከ12 ቀናት በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ዐቃቢ ህግ ሶስት ክሶችን የመሰረተበት የፍትህ መጽሄት ማኔጅንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥቅምት 11/2015 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ሁለቱ ክሶች ውድቅ የተደረጉለት ሲሆን በቀሪው በሶስተኛው ክስም ክርክር ላይ መሆኑ ይታወቃል። ጥቅምት 11/2015 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በነበረው ችሎትም ጠበቆች ሶስተኛው ክስ ዋስትና ስለማያስከለክል በሚል የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ጠይቀው ነበር። በእለቱም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከአሁን ቀደምም የዋስትና መብቱን የፈቀደለት መሆኑንና ነገር ግን የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ መከልከሉን አውስቶ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤት መውሰድ እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዚህም መሰረት የተመስገን ጠበቆች ጥቅምት 24/2015 የዋስትና መብቱ እንዲፈቀድለት ይግባኝ ማለታቸው ይታወሳል። የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን ተቀብሎ ዐቃቢ ህግ ምላሽ እንዲሰጥበት በሚል ለጥቅምት 30/2015 ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። በቀጠሮውም ዐቃቢ ህግ ምላሹን ይዞ ባለመቅረቡ እና ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍ/ቤቱን በመጠየቁ ለህዳር 1/2015 ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ ምላሹን በጽሁፍ ይዞ እንዲቀርብ ተለዋጭ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በስፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እንደተከታተለው በእለቱ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ እና ጠበቃ ቤተ ማርያም ተገኝተው እንደነበር ተመልክቷል፤ ነገር ግን የቂሊንጦ ማ/ቤት ተመስገን ደሳለኝን ፍ/ቤት አላቀረበውም። ዳኞችም በዋስትና ይግባኙ ጉዳይ የዐቃቢ ህግንና የጠበቆችን አቤቱታ ከተመለከቱ በኋላ ህዳር 1/2015 ውሳኔ ስለሚሰጡ ጠበቆች በእለቱ ከሰዓት በኋላ ወይም የፊታችን አርብ ህዳር 2/2015 ተገኝተው ውሳኔውን ማወቅ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply