You are currently viewing በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸምን የዘፈቀደ እስር እንደሚቃወሙ የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና 7 የተለያዩ ማህበራት አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ግንቦት 23 ቀን 201…

በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸምን የዘፈቀደ እስር እንደሚቃወሙ የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና 7 የተለያዩ ማህበራት አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 23 ቀን 201…

በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸምን የዘፈቀደ እስር እንደሚቃወሙ የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና 7 የተለያዩ ማህበራት አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና 7 የተለያዩ ማህበራት በጋራ ባወጡት አጭር መግለጫ በጋዜጠኞች ላይ የዘፈቀደ እስር እየተፈፀመ መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱን እንደሚቃወሙ ገልፀዋል። በመግለጨው ባለፉት 2 ሳምንታት 18 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በድንገተኛ ዘመቻ መታሰራቸውን ጠቅሰዋል። ጋዜጠኞች የህግ መተላለፍ ከተገኘባቸው እንደማንኛውም ዜጋ በፍትሃዊ የህግ ሂደት ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል። ይሁን እንጅ በየጊዜው በጋዜጠኞች ላይ በሚደረጉ እስሮች ላይ በተደጋጋሚ የህግ አግባብ ሲጣስ እየተስተዋለ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን አዋጅ ሕግ 1238/2013 አንቀፅ 86/1 ” በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የወንጀል ድርጊት በመፈፀም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በወንጀል ስነስርዓት ህግ ድንጋጌዎች መሰረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በአቃቤ ህግ አማካኝነት ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት” እንደሚል ጠቁመዋል። “ይሁንና የታሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች ምንም ክስ ሳይመሰረትባቸው ፣ ለቅድመ ክስ ምርመራ በሚሰጥ ቀጠሮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ከቤተሰብና ወዳጅ ጥየቃ ርቀው እንዲቆዩ እየተደረገ ነው” ሲሉ አካሄዱን አውግዘዋል። ይህ የህግ አግባብን ያልተከተለ አሰራር ፣ ለህግ የበላይነት ፣ ለሚዲያ ነፃነት ፣ ለጋዜጠኞች ደህንነት እና ለኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት አደጋ የሚፈጥር ስለሆነ አጥብቀን እናወግዛለን ነው ያሉት። የሚመለከታቸው አካላት በእስር ላይ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን አካላት በአስቸኳይ ከእስር ተለቀው የህግ የበላይነት እንዲከበር ሲሉ ተቋማቱ ጥሪ አቅርበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply