በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ ስርዓት እንደማይኖር የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃንን የመቆጣጠር እና አቅም የመገንባት ስልጣን ትልቁ የተቋሙ ተልዕኮ ሲሆን ከዚህ ቀደም በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሰራሮች ላይ ብዙ ቅሬታዎች ሲነሱ ቆይተዋል፡፡የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አንዷለም ለአሀዱ እንደገለፁት በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ አሰራር ሳይሆን ተቋማዊ ቅርፅን ይዞ አመራሮች ቢቀያየሩ የማይቀያየር ስርዓትን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ ወንደሰን አክለውም በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ ተቋም እንደይፈጠር መገናኛ ብዙሀን ገፍተው መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት እንዲሁም የጋዜጠኞችን መብት እና ነፃነት ከማስጠበቅ አንፃር ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየሰራ ነውም ብለዋበሰዎች ይሁንታ ላይ የተመሰረተ ተቋም እንዳይፈጠርም የሚዲያ ፖሊሲ ከማዘጋጀት አንስቶ የተለያዩ የለውጥ ስራዎች ተቋሙ እያከናወነ እንደሚገኝ ነው አቶ ወንደሰን የገለፁት፡፡

አዘጋጅ: ሰላም በቀለ

Source: Link to the Post

Leave a Reply