You are currently viewing በግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በስልሳው አካባቢ ሼህ መሀመድ አሊ ሀሰን የተባሉ አባት 8 ቤተሰቦቻቸው በአሸባሪው” ኦነግ ሸኔ በጥይት” ተገደሉባቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ሰኔ 13 ቀን…

በግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በስልሳው አካባቢ ሼህ መሀመድ አሊ ሀሰን የተባሉ አባት 8 ቤተሰቦቻቸው በአሸባሪው” ኦነግ ሸኔ በጥይት” ተገደሉባቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 13 ቀን…

በግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በስልሳው አካባቢ ሼህ መሀመድ አሊ ሀሰን የተባሉ አባት 8 ቤተሰቦቻቸው በአሸባሪው” ኦነግ ሸኔ በጥይት” ተገደሉባቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ስልሳው በሚባል ሰፈር በሚኖሩ አማራዎች ላይ ሰኔ 11/2014 ሙሉ ቀን በተፈጸመ የጅምላ ፍጅት ከ78 በላይ በቡድን መሳሪያ”ተጨፍጭፈ*ተገድለዋል።” ከእነዚህም መካከል ምንም እንኳ በአካባቢው ቀብር ለማስፈጸም የተላከው የጸጥታ አካል ከስርዓቱ ፖለቲካ በመነሳት የጅምላ*ቀብር እንዳይፈጸም መልዕክት ያስተላለፈ ቢሆንም ሰሚ አላገኘም። ምክንያቱም ሽህዎች ወደ ጫካ በመግባታቸው በአካባቢው ያሉት ሰዎች ብዙ ባለመሆናቸው የ61 ሰዎችን አስከሬን በአንድ ጉድጓድ ለመቅበር*ተገደዋል። በተጨማሪም በአንድ ቦታ 8፣ በሌላ አካባቢ ደግሞ 9 ሰዎች በጅምላ* ተቀብረዋል። በስልሳው (ጃተማ) አካባቢ በግፍ ከተገደሉት ከ78 በላይ አማራዎች መካከል “8 ቤተሰቦቼ በስናይፐር* ተገድለውብኝ ብቻዬን ቀርቻለሁ!” ያሉት ሼህ መሀመድ አሊ ሀሰን የተባሉ አባት ናቸው። በስራ ጉዳይ ድንገት ከመኖሪያ ቤታቸው የወጡት ሼህ መሀመድ አሊ ሀሰን ሲመለሱ አካባቢው የጦርነት* ቀጠና ሆኖ 8 ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካቶች በማንነታቸው ብቻ መጨፍጨፋቸውን ተመልክተዋል። የተገደሉት ቤተሰቦቻቸውም:_ 1) ወ/ሮ ኮኮቤ ሙሄ፣ 2) ጦይባ መሀመድ፣ (የ21 ዓመት ልጅ)፣ 3) የጦይባ መሀመድ የ4 ወር ህጻን፣ 4) ሰአዳ መሀመድ፣ የ14 ዓመት ልጅ ናት የ4ኛ ክፍል ተማሪ፣ 5) ሀሊድ መሀመድ የ11 ዓመት ልጅ፣_የ4ኛ ክፍል ተማሪ፣ 6) ሀያት መሀመድ_የ8 ዓመት ልጅ_የ2ኛ ክፍል ተማሪ፣ 7) ይስማ መሀመድ፣ የ5 ዓመት ሴት ልጅ እንዲሁም 8 ፋጢማ ኑሩ የተባለች የእንጀራ ልጃቸው ናቸው። በተመሳሳይ አብረው የተገደሉትም:_ 9) አህመድ ሰይድ፣ 10) 2 ሴቶች፣ 11) ደመቁ እንድሪስ፣ 12) የደመቁ እንድሪስ 2 ልጆች፣ እነዚህ 14 ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ በመትረጊዬስ እና በስናይፐር የተ*ገደሉ ናቸው። ስልሳው በተባለ አካባቢ ቤተሰባቸው በግፍ የተገደሉባቸው* አንድ አባት ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሲናገሩ “28 ሰዎችን በአንድ ላይ አሰልፈው ቤንዚን*አርከፍክፈው፣ በዲሽቃ*ደበደቧቸው፣ሰልፍ በማስያዝ አስተኝተው ነዳጅ አርከፍክፈው፣ ጨፍጭፈዋቸዋል*፤ ከ28ቱ መጨረሻ ላይ የተሰለፈችው አንሻ ሰይድ እጇን ቆስላ ተርፋለች፤ ወደ ህክምና ተወስዳለች፤ እሳቱ ሳይደርስባት ሞታለች* በሚል ጥለዋት ነው የሄዱት” ሲሉ የተፈጸመውን አሳዛኝ እልቂት ገልጸውታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply