በግሪክ ሁለት ባቡሮች ተጋጭተው 36 ሰዎች ሞቱ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-8dcd-08db1a2f40a4_cx0_cy9_cw0_w800_h450.jpg

በሰሜን ግሪክ አንድ የመንገደኞች መጓጓዣና ሌላ የጭነት ባቡር ዛሬ ተጋጭተው እስከ አሁን 36 ሰዎች ሲሞቱ 85 ቆስለዋል፡፡

በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዙ የነበሩት ሁለቱ ባቡሮች የተጋጩት ከመዲናዋ አቴንስ 380 ኪ.ሜ. ላይ ቴምፔ ሲሆን፣ ቢያንስ ሶስት ፉርጎዎች በእሳት ተቀጣጥለዋል፡፡

350 መንገደኞችን ከያዘው ባቡር ውስጥ፣ 250 የሚሆኑት መንገደኞች ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ወይም አነስተኛ ጉዳት እንደገጠማቸው ታውቋል፡፡

የአደጋ ሠራተኞች ፍርስራሹ ውስጥ ተቀብረው ሊኖሩ የሚችሉ ሰዎችን ለማዳን በመረባረብ ላይ ናቸው፡፡

66 ሰዎች ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ፣ ስድስቱ በጽኑ የተጎዱ መሆናቸውን የግሪክ እሳት አደጋ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ሁለቱ ባቡሮች ክፉኛ በመጋጨታቸው የአደጋ ሠራተኞቹን ሥራ ከባድ እንዳደረገው የእሳት አደጋ አገልግሎት ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply