በግብጽ ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 4 ህጻናትን ጨምሮ 11 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል፡፡
አደጋው የደረሰው በናይል ዴልታ አካባቢ በሚገኙ ሻሪዊያ እና አል ጋሪቢያ በተባሉ ግዛቶች ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ያደጋው መንስኤም በግብጽ የጣለው ከባድ ዝናብ ባሰከተለው ጎርፍ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
ጎርፉ በግብጽ ዋና ከተማ በካይሮ ጭምር ባሉ ዋና ዋና መንገዶችን ሲያጥለቀለቅና ለረዥም ጊዜ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መቋረጡም ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም ጎርፉ በመዲናዋ ባሉ የመሰረተ ልማት ላይም ጉዳት አድርሷል ተብሏል፡፡
ነዋወሪችም ለምን የሚቲዮሮሎጂ ባለሙያወች ቀድመው አደጋው እንደሚከሰት አልተናገሩም በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
በጅብሪል ሙሃመድ
ሕዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም
Source: Link to the Post