በግብፅ ቤተ ክርስቲያን በደረሰ የእሳት አደጋ 41 ሰዎች መሞታቸዉ ተሰማ፡፡በአገረ ግብፅ በአንድ የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን በደረሰ የእሳት አደጋ የ41 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 55 ሰዎች ጉዳት ደ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Y-wp2vKoOwNAlftWREpif63wKVb3N0XKEAok5L9fpzFObVISznwRZuA09D4Dx9eXdZ9uHuC1MpGXNAik6kpNkSgJ7CcrBBt2jUEnRo67SLhPlzqjkhPCdHIOi-4hVFzxuLobjNCxud_ywB10leY8LEKhCHo2Evy0ZvAsVDnfgDWuQuN3ClAEcokgQhsOxl4xF4HYJ_kLabnyrBBm2Y39sQNXCCJCaoeWYhD-0oX4eXr_eTTEqffZ6MK3QdiNtIsI3GAm2zifSTyoFreiCdMn17jSiegadlJFpeJmJBHMOG2bpwwAidFAsuCVhmYpGfJcSI9ocYkLzRtkJcVO9G3kww.jpg

በግብፅ ቤተ ክርስቲያን በደረሰ የእሳት አደጋ 41 ሰዎች መሞታቸዉ ተሰማ፡፡

በአገረ ግብፅ በአንድ የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን በደረሰ የእሳት አደጋ የ41 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 55 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

አደጋዉ የደረሰዉ ከዋና ከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘዉ ጊዛ ከተማ አቡ ሲፊን በተሰኘዉ የኮፐቲክ ቤተክርስቲያን ላይ ነዉ፡፡
የእሳት አደጋዉ በኤሌክትሪክ ምክንያት የደረሰ መሆኑም ታዉቋል፡፡

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በጥቃቱ የተሰማቸዉን ሀዘን ለአገሪቱ የኮፐቲክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ቴድሮስ 2ኛ መግለፃቸዉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
ግብጽ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ተመሳሳይ አደጋዎችን እያስተናገደች መሆኗን ዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

በአባቱ መረቀ

ነሐሴ 08 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply