በግዙፍነቱ ሁለተኛዉ የዑዝቤኪስታን የግብርና ማዳበሪያ ፋብሪካ ላይ ፍንዳታ አጋጥሟል፡፡ ከባድ የተባለው ፍንዳታ በናይትሮጅን ማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ውስጥ ማጋጠሙ ነው የተዘገበው፡፡ የዑ…

በግዙፍነቱ ሁለተኛዉ የዑዝቤኪስታን የግብርና ማዳበሪያ ፋብሪካ ላይ ፍንዳታ አጋጥሟል፡፡

ከባድ የተባለው ፍንዳታ በናይትሮጅን ማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ውስጥ ማጋጠሙ ነው የተዘገበው፡፡

የዑዝቤኪስታን ሁለተኛው ትልቁ የማዳበሪያ ፋብሪካ መሆኑ የተነገረለት ይህ ፋብሪካ ለሩስያ፣ ዩክሬን እና ኢራን ምርቶቹን ይልክ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ማክሳ ቺርቺክ ተብሎ የሚጠራው ይህ ፋብሪካ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ፍንዳታ ያጋጠመው ሲሆን ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ የዑዝቤኪስታን ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

በሰው ላይ ምንም አይነት የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ምላሽ አሰጣጥ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply