You are currently viewing በግፍ እስር ለሚገኙ ወገኖቻችንን በሙሉ ድምፅ እንሆን ዘንድ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥሪው አስተላለፈ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አ…

በግፍ እስር ለሚገኙ ወገኖቻችንን በሙሉ ድምፅ እንሆን ዘንድ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥሪው አስተላለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አ…

በግፍ እስር ለሚገኙ ወገኖቻችንን በሙሉ ድምፅ እንሆን ዘንድ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥሪው አስተላለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መምህርት ፣ ጋዜጠኛ እና ፀሀፊ መስከረም አበራ በዛሬው ዕለት ማለትም ታህሳስ 20/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት ትቀርባለች። የሃሰት ክሱም የሚከተለው ነው ፦ “ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በማሰብ በአዲስ አበባ እና በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን “ኢትዮ ንቃት “በተባለ የበይነ መረብ ሚዲያ እና የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም መንገድ እንዲዘጋ ማድረግ ፤ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት እንዳይታዘዝ በመቀስቀስ ወንጀል ነው ።” በተመሳሳይ የአማራ ተማሪዎች ፕሬዝዳንት እሸቱ ጌትነት ፣ ከእሱ ጋር የተያዘው መታገስ ፀጋ ፣የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) አመራር ፋኖ ጥላሁን አበጀ ፣የአርበኛ ዘመነ ካሴ አጃቢ ፋኖ ናትናኤል ዘነበ እና ኃይለማሪያም የተባለ ወጣት በግፍ እስር ገንዳ ውሃ ከተማ ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህ ወንድሞቻችን ነገ ታህሳስ 21/2015 ዓ.ም ገንዳ ውሃ ከተማ ፍ/ቤት ይቀርባሉ። የሃሰት ክሱም “ከፍተኛ የውንብድና ተግባር እና ዘረፋ” የሚል ክስ ነው። በመሆኑም በግፍ እስር ለሚገኙ ወገኖቻችንን በሙሉ ድምፅ እንሆን ዘንድ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥሪውን ያስተላልፋል። በማሰር ፣በማዋከብ እንዲሁም በመንግስታዊ አፈና የሚቆም ፥ የተጀመረ የአማራ ትግል የለም። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው። አማራነት ያሸንፋል!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply