You are currently viewing “በግፍ እስር ላይ ለምንገኘው ወገኖቻችሁ ድምጽ በመሆን ከእስር እንፈታ ዘንድ ከጎናችን አትለዩን” ሲሉ ባህር ዳር ላይ በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተከሰው የተፈረደባቸው የጦር መኮንኖች…

“በግፍ እስር ላይ ለምንገኘው ወገኖቻችሁ ድምጽ በመሆን ከእስር እንፈታ ዘንድ ከጎናችን አትለዩን” ሲሉ ባህር ዳር ላይ በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተከሰው የተፈረደባቸው የጦር መኮንኖች…

“በግፍ እስር ላይ ለምንገኘው ወገኖቻችሁ ድምጽ በመሆን ከእስር እንፈታ ዘንድ ከጎናችን አትለዩን” ሲሉ ባህር ዳር ላይ በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተከሰው የተፈረደባቸው የጦር መኮንኖች ለመላው የአማራ ሕዝብ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል የባለስልጣናት የግድያ ወንጀል እና ህገ መንግስቱን በሃይል ልትንዱ ነበር ተብለው ተከሰው እና ተፈርዶባቸው በባህር ዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ የጦር መኮንኖች ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነትና ሉዓላዊነት መከበር ከፍተኛ የሆነ ዋጋ የከፈሉ ስለመሆናቸው አውስተዋል። የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን የገለጹት የጦር መኮንኖች ከዚህ በፊት በሀገር መከላከያ ሠራዊትም በሌሎችም የፀጥታ ቢሮዎች ውስጥ ሲሰሩ እንደነበሩ ህዝብ ይወቅልን በማለት ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በላኩት ደብዳቤ አውስተዋል። ነገር ግን በወያኔ የግፍ ስርዓት ወቅት በአማራነታቸው ብቻ ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከሌሎችም የፀጥታ ቢሮዎች በማንነታቸው ተገፍተው የወጡ ስለመሆናቸውም ጠቁመዋል። አስከፊውን የወያኔ ስርዓት በመቃወም እና ፊት ለፊት በመጋፈጥ ኤርትራ በረሃ ድረስ በመግባት ለአማራ ሕዝብ ነፃነት እና ለኢትዮጵያ አንድነት መከበር መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች ያሉበት ስብስብ ስለመሆኑም ገልጸዋል። በወያኔ አሰቃቂ ስርዓት ውስጥም ልክ እንደ እነ አምሳ አለቃ አበበ መልኬ ያሉ በማዕከላዊ ፣ በቃሊቲ እና በዝዋይ እስር ቤቶች ለሰባት (7) ዓመት በእስር ያሳለፉም ይገኙበታል። ብ/ጄ አሳምነው ፅጌ ወደ አማራ ክልል የፀጥታ ቢሮ ሲገባ የአማራን ሕዝብ ከጥቃት እና ግድያ እንዲሁም ከመፈናቀል እና ወረራ ለመታደግ ፀጥታውን ለማጠናከር በተደረገው ጥሪ መሰረትም ወደ ፀጥታው ተቀላቅለው ሕዝብን ከሚደርስበት ጭቆና የታደጉ ጀግኖች ስለመሆናቸው ተመላክቷል። ከየአቅጣጫው በአጭር ግዜ በመሰባሰብ በብር ሸለቆ ፣በጃሬ እና ፣በአመድ በር ማሰልጠኛዎች ልዩ ኃይል በማሰልጠን እና በማደራጀት እንዲሁም በመምራት ትልቅ ሚና እንደነበራቸው በደብዳቤው ተጠቁሟል። የህወሓትን ወረራ በመመከት በኩል ያሰለጠኑት ሃይል ትልቅ ድርሻ እንደነበረው በማውሳት ይህም የማይካድ ሃቅ ነው ሲሉ ገልጸውታል። በቤንሻንጉል መተከል ዞን ፣ በጭልጋ፣ በከሚሴ እና በሌሎች አካባቢዎች የአማራ ጭፍጨፋን እና ጥቃትን ለመመከት እና ለመከላከል እንዲሁም ቀድሞ ችግሮችን በመለየት እና በማጥናት ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ስራ የሰሩ ጀግኖች ያሉበት ስብስብ ስለመሆኑም ሁሉም የአማራ ተቆርቋሪዎች ሊያውቁት ይገባል ብለዋል። የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆችን በማሰር፣ እንደነ ብ/ጀ አሳምነው ፅጌ ያሉትን ህይወታቸውን በማጥፋት አማራን ለውርደት፣ ለስቃይ እና ለባርነት ለመዳረግ ታስቦ እየተሰራ እንደሆነ መታወቅ እንዳለበት ጠቁመዋል። በመሆኑም በውጭ ሀገራት ያሉ የአማራ ምሁራን ፣ለአማራ ሕዝብ ነፃነት እየተጉ ያሉ ድርጅቶች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ያሉ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች ጠንካራ ትግል በማድረግ እና በመንግሥት ላይ ጫና በማሳደር ከእስር ቢለቀቁ ቢደረግ ለሕዝብ ኩራት እንደሚሆኑ በደብዳቤው ተገልጧል። በእስር ላይ ያሉ ጀግኖችን ባሰብን ቁጥር ለአማራ ሕዝብ ሲል ውድ ህይወቱን የሰጠውን ብ/ጄ አሳምነው ፅጌን እያሰብን እንደሆነ ሁሉም አማራ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል። ትክክለኛ የብ/ጄ አሳምነው ፅጌ ልጆች ያሉትና የእሱን ራዕይ በትክክል የተረዱ እና የተማሩ ጀግኖች እንዳሉበት ሁሉም አማራ ሊረዳ እንደሚገባውም በደብዳቤው ተመላክቷል። ለሀገራቸው ዕድሜ ዘመናቸውን ዋጋ ከመክፈል ውጭ ምንም እንከን እንደማይገኝላቸው፣ ለጥቅም እና ለፖለቲካ ነጋዴነት ያልቆሙ ይልቁንም እነሱም ሆነ ቤተሰቦቻቸው በስቃይ ውስጥ እንዳሉ የአማራ ተቆርቋሪዎች እወቁልን ብለዋል። በሰኔ 15ቱ የግድያ ክስ ጉዳይም በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 03-06-2014 ዓ.ም እና በ29-06-2014 ዓ.ም በወ/ህ/ቁ 27/1/፣32/1/ሀ/፣ 35፣38 እና 238/2/መሰረት የጥፋተኝነት ፍርድ በመስጠት በሌሉበት ጉዳያቸው ሲታይ ከነበሩት ውስጥ:_ 1) ሻምበል መማር ጌትነት፣( ነፍስ ይማር) 2) በላይሰው ሰፊነው፣ 3) ልቅናው ይሁኔ በተባሉት ላይ በእያንዳንዳቸው በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የተደረገ ሲሆን፣ 4) ሻምበል ውለታው አባተ በ16 ዓመት፣ 5) ሻለቃ አዱኛ ወርቄ በ17 ዓመት፣ 6) ሻምበል ታደሰ እሸቴ በ17 ዓመት፣ 7) አምሳ አለቃ አበበ መልኬ በ16 ዓመት፣ 8 አምሳ አለቃ በላቸው ዘውዴ በ15 ዓመት፣ 9 አምሳ አለቃ አሰፋ ጌታቸው በ16 ዓመት ከ6 ወር፣ 10) አምሳ አለቃ አየነው ታደሰ በ16 ዓመት ከ6 ወር፣ 11) ሳጅን መልካሙ ባለሟል በ16ዓመት ከ6ወር፣ 12) ኮንስታብል ሙሉጌታ ፀጋየ በ18 ዓመት፣ 13) አስር አለቃ አያልነህ ገዛሀኝ በ16 ዓመት ከ6 ወር፣ 14) ወ/ር ብርሃኑ ይደጉ በ16 ዓመት ከ6 ወር፣ 15) አስር አለቃ ፈንታሁን እንድሪስ በ16 ዓመት ከ6 ወር፣ 16) አምሳ አለቃ አሊ ሃሰን በ18 ዓመት፣ 17) አምሳ አለቃ ሲሳይ ገላነው በ15 ዓመት፣ 18) አምሳ አለቃ ፍቃዱ ምትኩ በ18 ዓመት፣ 19) አስር አለቃ በለጠ ወርቁ በ16 ዓመት ከ6ወር፣ 20) አስር አለቃ አሸናፊ ዳኛ በ16 ዓመት ከ6ወር፣ 21) ወ/ር ይመር እሸቱ በ16 ዓመት ከ6ወር፣ 22) ወ/ር እሸቴ ስዩም በ16 ዓመት ከ6ወር፣ 23) ምክትል አስር አለቃ ምስጋናው ገነት በ16 ዓመት ከ6ወር፣ 24) አስር አለቃ አባተ ብዙአየሁ፣ በ18 ዓመት፣ 25) ወ/ር መንግሥቱ መኩሪያው በ16 ዓመት ከ6ወር፣ 26) ወ/ር መለስ መብራቱ በ16 ዓመት ከ6 ወር፣ 27) አምሳ አለቃ ጥጋቡ ለገሰ በ16 ዓመት ከ6ወር፣ 28) ምክትል አስር አለቃ አሊ ኢብራሂም በ16 ዓመት ከ6 ወር፣ 29) ወ/ር መንግሥቱ እያሱ በ16 ዓመት ከ6ወር፣ 30) አምሳ አለቃ ልመንህ የኔሰው በ16ዓመት ከ6ወር እንዲሁም 31) አስር አለቃ ጉልሽ ደምሳሽ በ16 ዓመት ከ6ወር ጽኑ እስራት፣ ያለበደላቸው በግፍ ተፈርዶባቸው በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የጦር መኮንኖች ሲቀጥሉ ይህ የግፍ ፍርድ አልበቃ ብሎ፣ 1ኛ) ታረቀኝ አረጋ እና 2ኛ) ሁሉስም አዲላ የተባሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ባልደረቦች፣ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጡልኝ በማለት ይግባኝ ብለውብናል ነው ያሉት። ወደ ሁለት ግዜ ቀጠሮ በመስጠትም የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን መርምሮ መዝገቡ ያስቀርባል በማለት ሂደቱ ቀጥሎ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በመጨረሻም “በግፍ እስር ላይ ለምንገኘው ወገኖቻችሁ ድምጽ በመሆን ከእስር እንፈታ ዘንድ ከጎናችን አትለዩን” ሲሉ ባህር ዳር ላይ በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተከሰው የተፈረደባቸው የጦር መኮንኖች ለመላው የአማራ ሕዝብ ጥሪ አድርገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply