You are currently viewing በግፍ እስር ላይ የሚገኘው መምህርና የማህበራዊ አንቂው ግርማ አየለ ሰኔ 28 /10/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት ይቀርባል‼ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በግድያ ወንጀል ተጠ…

በግፍ እስር ላይ የሚገኘው መምህርና የማህበራዊ አንቂው ግርማ አየለ ሰኔ 28 /10/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት ይቀርባል‼ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በግድያ ወንጀል ተጠ…

በግፍ እስር ላይ የሚገኘው መምህርና የማህበራዊ አንቂው ግርማ አየለ ሰኔ 28 /10/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት ይቀርባል‼ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ያለምንም ፍትህ ወራትን ያስቆጠረው መምህርና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂው ግርማ አየለ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በባህርዳርና አካባቢዎች ፍ/ቤት እንደሚቀርብ ታውቋል። በማሕበራዊ ሚዲያ በአማራ ፖለቲካ በተፅኖ ፈጣሪነቱ ፋናወጊ ከሚባሉ ወጣቶች አንዱ የሆነው መምህር ግርማ አየለ በግል ቂም አንድ ባለስልጣን የግል እስረኛ እንዳደረገው እየተነገረ ነው ። የብልፅግና የጡት አባት ኢህአዴግ በመጨረሻዎቹ የስልጣን ዘመኑ ይህን አይነት ስትራቴጅ ይከተል እንደነበር የገለፁት የአሻራ ምንጮች ተረኛው የብአዴኑ ብልፅግና የነቁ የአማራ ማህበራዊ አንቂወችንና፣ ጋዜጠኞችን እና በመተከልና እና በወለጋ የሚጨፈጨፈውን የአማራ ተወላጅ የሚደርስበትን የዘር ፍጅት ለህዝብ ስለሚያሳውቁ ወደ ወህኒ ቤት ይወረወራሉ። ግርማ አየለ እና መሠል የነቁ የአማራ ማህበራዊ አንቂዎች በወለጋ የተፈጠረውን የአማራ ተወላጆች ጭፍጨፋ እና በየእስር ቤቱ የሚገኙ ፋኖዎች አብዝተው ስለ ፍትህ ስለሚጮሁ ብልፅግና ስርዓት ካድሬዎቹ ስልጣናቸውን በመጠቀምወጣቱን እያፈሱ የቂም መበቀያ እያደረጉ መሆኑ እየተገለፀ ይገኛል። ህዝብን በማሰር እና በማፈን የሚመጣ ለውጥ ስሌለለ ቀልበችሁን ወደ ማህበረሰቡ ሰብሰብ አድርጋችሁ ለህዝባችሁ ብታገለግሉ ታተርፋለችሁ እንጂ አትጎዱም ሲሉ የአሻራ ምንጫችን ተናግረዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply