You are currently viewing በግፍ እስር ላይ የሚገኘው አርበኛ ዘመነ ካሴ እና በሽህ የሚቆጠሩ ፋኖዎች እስካልተፈቱ ድረስ በቅርቡ ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ትግል በተጠንቀቅ እና በመወያየት እንዲጠብቀን ሲሉ የአማ…

በግፍ እስር ላይ የሚገኘው አርበኛ ዘመነ ካሴ እና በሽህ የሚቆጠሩ ፋኖዎች እስካልተፈቱ ድረስ በቅርቡ ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ትግል በተጠንቀቅ እና በመወያየት እንዲጠብቀን ሲሉ የአማ…

በግፍ እስር ላይ የሚገኘው አርበኛ ዘመነ ካሴ እና በሽህ የሚቆጠሩ ፋኖዎች እስካልተፈቱ ድረስ በቅርቡ ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ትግል በተጠንቀቅ እና በመወያየት እንዲጠብቀን ሲሉ የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) እና የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አርበኛ ዘመነ ካሴን ለማስፈታት የተደረገውን የመጀመሪያ ምዕራፍ የሚዲያ ዘመቻ ማጠናቀቂያ እና በቀጣይ የሚደረጉ የትግል አቅጣጫዎችን በተመለከተ ከአወማ እና አተማ የተሰጠ መግለጫ! እንደሚታወቀው “ፍትህ ለአርበኛ ዘመነ ካሴ” በሚል መሪ ቃል ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሚዲያ ዘመቻ በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል። አርበኛ ዘመነ ካሴ ከስድስት ወራት በላይ ያለምንም ፍትህ ፣ያለ አግባብ እና በግፍ እስር በሰባታሚት ማረሚያ ቤት እየተሰቃየ ይገኛል። ከሰሞኑ የአማራ ክልላዊ መንግስት አርበኛ ዘመነ ካሴን ይቅርታ ጠይቆ ለመልቀቅ የወሰነ ቢሆንም በተወሰኑ አድርባይ ፣የጠላት ተልዕኮ አስፈፃሚ እና ህዝባችንን ለመከፋፋል የሚሰሩ ጥቂት ተላላኪዎች፣አድርባዮች ለመፍታት የወሰኑትን ውሳኔ ከጠላት ተልዕኮ በተቀበሉ የክልሉ ሹማምንት ውሳኔው ተግባራዊ እንዳይሆን ከፍተኛ ጫና በማድረጋቸው ፤ውሳኔውን በማጠፋቸው እስከ ዛሬ ድረስ አልተፈታም። ስለሆነም መሪያችንን ፣ምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴን ለማስፈታት የመጀመሪያውን የትግል ምዕራፍ ማለትም “ፍትህ ለአርበኛ ዘመነ ካሴ” የሚዲያ ዘመቻ ከተባባሪ የሚዲያ አካላት እንዲሁም በንቃት ከተሳተፉ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ጋር በመሆን በጥሩ ሁኔታ ዛሬ ተጠናቋል። አርበኛ ዘመነ ካሴ በልጅነት እድሜው ስርዓተ መንግስቱ ለፍትህና እኩልነት ያልቆመ መሆኑንን ተርድቶ ፣አሁን በዙፋን ላይ ዙፋን የደረቡት ከንቱዎች ስልጣን ለመቆናጠጥ በሚታትሩበት ወቅት ስርዓተ መንግስቱ የሰጠውን የስልጣን ድርጎ አሽቀንጥሮ በመጣል ፤በህዝባችን ለቅሶ ላይ የሚ የምቀበለው ዙፋን ፤የማጣጥመው የደስታ አዝመራ የለም በማለት የአባቶቹን ነፍጥ አንስቶ ጫካ የገባ ጀግና አርበኛ ነው። ዘመነ ካሴ የአማራን ህዝብ የማያከብር ፣ለስልጣን መቆናጠጫ ብቻ የሚፈልጉትን “የአንድነት ሀይሎች ፥በኢትዮጵያዊነት ካባ የተሸፈኑ የአማራ ህዝብ ድብቅ ጠላቶች” ጋር የሚደረግ የትግል ጉዞ ቀድሞ የገባው የእኛ ዘመን ንቁ ፣ብቁ አማራ ትውልድ ነው፤ አርበኛ ዘመነ ካሴ የሁሉንም ወሰን ያውቃል። “ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም” የሚል ድንቅ መርህ ያለው ሚዛናዊ ፣ፍትሃዊ እና አስተዋይ መሪ ነው። መናገር ሲጀምር ማዳመጥ አልፈልግም የሚል ሰው ካለ እንኳን ከልብ የሚደመጥ አንደበተ ርዕቱ ነው። አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ ከ12 ሺህ በላይ የነቁ አማራዎች ያለምንም የወንጀል ጭብጥ ሲታሰሩ ፣ሲታፈኑ እና ሲሳደዱ ማህበረሰቡ ላይ ያሳዳረው ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ቀላል አይደለም። አርእያ አድርጓቸው የሚንቀሳቀሰው ወጣቱ ክፍልም ምልክት አልባና ተቅበዝባዥ የመሆን እድሉ ከፍ ያለ ነው። የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) እና የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ):_ አርበኛ ዘመነ ካሴ እንዲለቀቅ የመጀመሪያ ምዕራፍ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲያጠናቅቅ እና ቀጣዩን የትግል ምዕራፍ ተቋማዊ አድርጎ ሲያስጀምር የማህበረሰቡን ስነ ልቦናዊ ጉዳት እና ማህበራዊ ቀውስ የመከላከል ፣የትውልዱን ምልክት የመጠበቅ ሲቪክነት ሃላፊነቱን ለመወጣት ነው። በመሆኑም:_ 1) አርበኛ ዘመነ ካሴ በአንድ ሳምንት ውስጥ የማይለቀቅ ከሆነ ፣ 2) ከ12 ሺህ በላይ የነቁ አማራዎች ከታፈኑበት የማይለቀቁ ከሆኑ እንዲሁም 3) በአሁኑ ወቅት መንግስት ከአሸባሪዎች ጋር የሚያደርገውን ልክ አልባ መስተፋቅር የአማራን ህዝብ የርስትና የማንነት ጥቅም የሚያሳጣ ከሆነ ፣ 4) የአማራን ህዝብ ተፈጥሮዊ እሴት የፋኖ ተቋምን ለማፍረስ እና የአማራን ህዝብ እንደ አሁን ቀደሙ ለጠላቶቻችን አስሮ ለመስጠት የሚያደርገውን አደገኛ እንቅስቃሴ የማይገታ ከሆነ፣ አባሎቻችን ፣መላውን የአማራን ህዝብ እንዲሁም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አስተባብረን ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ትግል የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን። በመሆኑም መላው ህዝባችን በቅርብ ቀናት ውስጥ ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ትግል ፣ህዝባዊ ንቅናቄ በተጠንቀቅ እና በመወያየት እንዲጠብቀን የከበረ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ። በመሆኑም ዝርዝር አፈፃፀሙን እና ተግባራትን በተለያዩ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች በቅርብ ቀናት የምናደርስ ይሆናል። ሁሉም በያለበት የሚደርሰውን መረጃ በንቃት ይጠብቅ። ለተግባራዊነቱ ራሱን በመንፈስ ፣ በስነ ልቦና ወዘተረፈ በሁሉም ረገድ ራሱን ያዘጋጅ ። የአርበኛ ዘመነ ካሴ ወንጀል ለአማራ ህዝብ ነፃነት ፣ፍትህ እና እኩልነት መቆሙ ነው ። መላው ህዝባችን ይህንን ጀግና የማስፈታት ታሪካዊ ግዴታ አለብን ። በማሰር የሚቆም ፣የተጀመረ የአማራ ትግል የለም ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። ክብራችንን በክንዳችን!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply