
በግፍ እስር ላይ የነበሩት አቶ ካሳሁን ደስታ እና አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እያንዳንዳቸው በ10 ሽህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ፍ/ቤቱ ወሰነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እና የፓርቲው ንቁ አባልና ጉዳይ አስፈፃሚ አዲስ አበባ ውስጥ ታህሳስ 3/2015 ዓ.ም. በፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህ በግፍ እስር ላይ የነበሩት አቶ ካሳሁን ደስታ እና አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እያንዳንዳቸው በ10 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍ/ቤቱ መወሰኑን ባልደራስ አስታውቋል።
Source: Link to the Post